1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴት ልጅ ግርዛት በኬንያ

ማክሰኞ፣ ጥር 29 2010

ዛሬ የሴቶችን ግርዛት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወገዝበት ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በአውሮፓ ከተሞች ጭምር ታስቦ ውሏል፡፡ በኬንያ ግን የሴት ልጅ ግርዛት በሃኪሞች ታግዞ ሊከናወን ይገባል የሚሉ አንዲት ተሟጋች ተነስተዋል።

https://p.dw.com/p/2sD9M
Symbolbild FGM
ምስል picture alliance/dpa/EPA/UNICEF/ASSELIN

የሴት ልጅ ግርዛት በኬንያ

ከ200 ዓመት በፊት ባርነት በብዙ አካባቢ ተከልክሏል፡፡ ከእርሱ ጋር እስረኛን መግረፍ እና ማሰቃየት እንደዚሁ በህግ ወንጀል ነው ተብሎ በዓለም ዙሪያ ታግዷል፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲሞከራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች በመጨረሻው እንዲታወጅ በር ከፍቷል፡፡ ይህ አዋጅ በስራ ላይ ከዋለ ብዙ ዓመታት አልፎታል፡፡

የሴቶችን መብት የሚያውቀው ህግ ደግሞ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ህጻናት ልጆችን እና ወጣት ልጃገረዶች እንዳይገረዙ በህግ ከልክሏል፡፡ ይህም ከሆነ እንደዚሁ ሰንበት ብሏል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎች የሴቶችን ግርዛት ያላንዳች ርህራሄ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቃወሙበት ቀን ታውጇል፡፡ ይህ ቀን በዓለም ዙሪያ፤ በአውሮፓ ከተሞች ጭምር፤ ዛሬ ታስቦ ውሏል፡፡ 

ዘጋቢያችን አንድሪው ቫሲክ ግን ኬንያ ላይ ከሴት ልጅ ግርዛት ጋር በተያያዘ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡ የሴት ልጅ ግርዛት በሃኪሞች ታግዞ ሊከናወን ይገባል የሚሉ አንዲት ተሟጋች ተነስተዋል። ይልማ ሀይለሚካኤል ያጠናቀረውን የቫሲክ ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡ 

ይልማ ሀይለሚካኤል

ሂሩት መለሰ