1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስላም ስምምነትና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ምላሽ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2003

የኢትዮዽያ መንግስት ከአንድ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር አንጃ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። በአድሚራል ሞሀመድ ኦማር ሀሰን የሚራው የኦብነግ ክፍል ስምምነቱን ፋይዳ የሌለው ሲል አጣጥሎታል።

https://p.dw.com/p/PdTe
ምስል AP

ትላንት የኢትዮዽያ መንግስት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል። አንደመንግስት መግለጪያ ከሆነ ትላንት ስምምነቱን የተፈራረመው አንጃ የግንባሩን 80 ከመቶ የሚወክል ነው። በሌላ በኩል በአድሚራል ሞሀመድ ኦማር ሀሰን የሚመራው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር የትላንቱን ስምምነት ተቀባይነት የሌለው፤ ለሰላም አንዳች ፋይዳ የማይኖረው ሲል አስታውቋል። የግንባሩ የኢትዮዽያ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የተፈጸመ ነው። ከግንባሩ ከ6 ዓመት በፊት የተባረሩት ግለሰብ ግንባሩን አይወክሉም ብለዋል። መሳይ መኮንን አቶ ሀሰን አብዱላሂን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ