1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስልጣን ሽግሽግ ለሙጋቤ ተከታይ

እሑድ፣ ኅዳር 28 2007

ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ባለቤታቸዉን የዚምባቡዌ ቀጣይ የሀገር አስተዳዳሪ ለማድረግ በእጩነት አበቁ። ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን የገዢው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሀራሬ ውስጥ ባካሄደው ስብሰባ የ49 ዓመቷን ወ/ሮ ከሴቶች ክፍል ተጠሪ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ግሬስ አንዱን ቀን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚሹም አመላክተዋል።

https://p.dw.com/p/1E0Wg
Präsident Robert Mugabes Grace Mugabe steigt in Parteiführung auf
ምስል Reuters/Philimon Bulawayo

የ90 ዓመቱ ባለቤታቸው ሮበርት ሙጋቤ፤ ከዓለም ሃገራት ፕሬዚዳንቶች በእድሜ አንጋፋው መሪ መሆናቸዉ ይታወቃል። የሙጋቤ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆይስ ሙጁሩ በፓርቲው ስብሰባ ላይ እንዳልተገኙ ተገልጿል።

የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በእሳቸዉና በፓርቲያቸዉ ላይ የሚያሴሩ ያሏቸዉን ባለሥልጣናትን እንደማይምሩ መዛታቸዉ ይታወቃል። ሙጋቤ ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ለተሠየመዉ የዚምባቡዌ ገዢ ፓርቲ ዛኑ-ፒ ኤፍ ጉባኤ ባለፈዉ አርብ እንደነገሩት ወንጀል የፈፀሙ፤ በአመራራቸዉ አንፃር የሚያሴሩና በሙስና የተዘፈቁ ባለሥልጣናት ከሥልጣን ይወገዳሉ፤ በሕግም ይጠየቃሉ። ዚምባቡዊዉን ከነፃነት ጀምሮ ላለፉት ሠላሳ አራት ዓመታት የመሩት የዘጠና ዓመቱ አዛዉንት ምክትላቸዉንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይተኳቸዋል ተብለዉ የሚጠበቁትን ምክትል ፕሬዝዳንት ጆይስ ሙጁሩን ጉባኤዉ ከተከፈተ ጀምሮ በግልፅ እያወገዟቸዉ ነበር። ሙጁሩና ተባባሪዎቻቸዉ ባለሥልጣናት በጉባኤዉ አልተካፈሉም። የጋራ ብልፅግና ጥናት ተቋም አጥኚ ሱ ኦንስሎዉ እንደሚሉት የሙጋቤ ዉግዘትና ርግማን ሙጁሩንና ተባባሪዎቻቸዉን አግልለዉ ሥልጣናቸዉን አንድም ለቤታቸዉን ለግራስ ሙጋቤ አለያም ለሌሎች የቅርብ ታማኞቻቸዉን ለማዉረስ ማቀዳቸዉን ጠቋሚ ነዉ።«ይሕ በዛኑ-ፔ ኤፍ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊ ሽኩቻና አንጀኝነት ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን አመልካች ነዉ።ሙጋቤ ለፓርቲ መሪነት ያለምንም ተቀናቃኝ መመረጣቸዉ አያጠያይቅም። ይሁንና የዘጠና ዓመት አዛዉት በመሆናቸዉ እሳቸዉን ለመተካት የሚደረገዉ ፍልሚያ እጅግ ተፋፍሟል። ባለቤታቸዉ ግራስ ሙጋቤ ከፍተኛ የሥልጣን ጉጉት እንዳላቸዉ የማያጠራጥር መሆኑም ተመልክቶአል። የጆይስ ሙጁሩ የምክትል ፕሬዝዳንት ሥልጣን ደግሞ የነፃነት ታጋይ የነበሩት ባለቤታቸዉ ሶሎሞን ሙጁሩ ከሞቱ ወዲሕ በጅጉ ተመናምኗል።»ሙጁሩ የተሰነዘረባቸዉን ዉንጀላ አስተባብለዋል። ንፁሕነታቸዉን በፍርድ ቤት ጭምር ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል። የሙጋቤን አቋም በመቃወም የፓርቲዉ ቃል አቀባይ ሥልጣን ሲለቁ፤ ሁለት ሚንስትሮችም በጉባኤዉ አልተካፈሉም። 12 ሺሕ የዛኑ ፒ ኤፍ ከፍተኛ ካድሬዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ እሁድ አብቅቷል።

Grace Mugabe
ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤምስል J. Njikizana/AFP/Getty Images

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ