1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስዌቶዉ የማንደላ የቀድሞ ቤት

ዓርብ፣ ሰኔ 21 2005

የ 94 ዓመቱ ደቡብ አፍሪቃዊ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ ኔልስን ማንዴላ ዛሬም በጠና እንደታመሙ ነዉ። ሆኖም ዛሬ ከቀትር በኋላ የቀድሞ ባለቤታቸው ዊና ማንዴላ ፣ የማንዴላ የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።

https://p.dw.com/p/18yGh
Tittle: Foto von der Wellwisher-Wall außerhalb der Klinik von Äthiopiern zu Mandela Autor/C: DW/Ludger Schadomsky Zulieferer: Shewaye Legesse
ምስል DW/L. Schadomsky

በርካታ ደቡብ አፍሪቃዉያን እና ቱሪስቶች ለማንዴላ ያላቸዉን ፍቅር እና ክብር ለመግለጽ እሳቸዉ በተኙበት በፕሪቶርያዉ ሆስፒታል እና አካባቢዉ ብቻ ሳይሆን፤ በስዌቶ አንጋፋዉ የነጻነት ታጋይ ይኖሩበት ወደነበረዉ የአሁኑ ቤተ መዘክር፣ በመጉረፍ ላይ ናቸዉ።በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪቃ ትምህርት ቤት ተዘግቶ የእረፍት ጊዜ ቢሆንም፤ በርካታ ተማሪዎች በስዌቶ ምዕራብ ኦርላንዶ መንደር በምትገኝ አንድ ጠባብ መተላለፍያ ወደ ቤት ቁጥር 8115 ሲያልፉ ይታያል። ለወትሮ ጫጫታና ወሬ የማያጣቸዉ እነዚህ ተማሪዎች፤ በክብርና በፀጥታ ለዚህ ጉብኝት እንደተዘጋጁ መምህራቸዉ ይገልጻሉ።«ማንዴላ ሆስፒታል ስለተኙ፤ ምንም እንኳ የእረፍት ግዜ ቢሆንም፤ ቤታቸዉን ለመጎብኘት ወሰንን። ህጻናቱ በትምህርት ቤት ስለማንዴላ ብዙ ነገሮችን ነዉ የሚማሩት።» ደቡብ አፍሪቃዉያን ፓፓ ወይም ታታ እያሉ የሚጠሩዋቸዉ የቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ለሕጻናቱ ማን ናቸዉ?

3. Bildtitel: Schulklasse in Mandela House Museum Schlagworte: Mandela, Schulklasse, Museum, Pretoria Wer: Ludger Schadomsky Wann: 27.6.2013 Wo: Pretoria, Südafrika Zulieferer: Lina Hoffmann
ምስል DW/L. Schadomsky

«ነጻ አዉጥተዉናል እና ዛሬ በጣም እንደምንወዳቸዉ ልንነግራቸዉ እንሻለን» «ለኔ ጀግናዬ ናቸዉ። ምክንያቱም ለነፃነት ተፋልመዋልና።» «ለኔ እንደ አባት ናቸዉ። ማንዴላን እወዳቸዋለሁ። እጅግ በጣም እወዳቸዋለሁ።» «ለሰዎች የሚያስቡ ሰዉ ናቸዉ። ለሕፃናትም ለሌሎች ሰዎችም ደግ ናቸዉ። ይወዱናል።» «ኦ,, ጀግና እና ለእያንዳንዱ ሰዉ ምሳሌ ናቸዉ። እዚህ ለአብዛኞች እንዲሁም ለኛ በጣም ትልቅ ሰዉ ናቸዉ እናም በቶሉ እንዲሻላቸዉ እንመኛለን። የጤንነታቸዉ ሁኔታ ይሻሻላል የሚል ተስፋ አለኝ»

ህጻናቱ አስጎብኝዋን እየተከተሉ ቤተ መዘክሩን ይመለከታሉ። የነፃነት ተምሳሌት የሆኑት ማንዴላ ለ15 ዓመታት ያህል ኖረዉበታል። «የምንገኘዉ በዓለም እጅግ ታዋቂ በሆኑት በኔልሰን ማንዴላ ቤት ዉስጥ ነዉ። ማንዴላ የመንግስት ሚስጥር በማባከን ወንጀል ተከሰዉ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ ወህኒ ከመዉረዳቸዉ በፊት የኖሩት እዚህ ነበር»በማንዴላ የቀድሞ ቤት ለእይታ ከቀረቡት መካከል በተለይ አልጋቸዉ፤ ለቀድሞዉ ቦክሰኛ እና ትከሻ ሰፊዉ ሰዉ እጅግ ጠባብ ይመስላል። እንደ ቤተ መዘክሩ አስጎብኝ ገለፃ፤ ማንዴላ በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ከእስር ሲለቀቁም ወደቤታቸዉ ተመልሰዉ እዚሁ አልጋ ላይ ነበር ይተኙ የነበረዉ ግን ብዙም አልቆዩ፤ «እንደኔ እምነት ከ 27 ዓመታት እስር በኋላ፤ ምን ያህል ታዋቂ እንደሆኑ የገባቸዉ አልመሰለኝም። እዚህ ቤት ተመልሰዉ ኖረዋል ግን የቆዩት 11 ቀናት ብቻ ነበር። ይታያችሁ እናንተ እዚህ ተኝታችሁ ወይm ቁጭ ብላችሁ ልክ አሁን እንደእናንተ በርካታ ህዝብ እና የመገናኛ ብዙሃን በቀን በቀን ሲመጣ,,,, እናም በዚህም ምክንያት ይህን ቦታ ለቀዉ ወጡ»

አሁን የቀድሞ ቤታቸዉን ለመጎብኘት ከተለያዩ ሃገራት በርካቶች ይመጣሉ። ከጀርመን፤ ካልስሩወ ከተማ ወደ ደቡብ አፍሪቃ የመጡት ዮሃን ሪትዝማን አገሪቱን ሁለት ሳምንታት ሲጎበኙ ቆይተዋል። የማንዴላን የቀድሞ ቤት እየጎበኙ እንዲህ አሉ፤ «እንደ እኔ እምነት በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪቃ አንድ ታሪክ እየተጻፈ ነዉ። ማንዴላ ሲያሸልቡ መላ አፍሪቃ ልቧ የሚነካ እና አንድ ልዩ ቀን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። የምመኝ ላቸዉና ተስፋም የማደርገዉ እጅግ እንዳይሰቃዩ ነዉ።»

Candles burn alongside a photograph of Nelson Mandela outside the Medi-Clinic Heart Hospital, where the ailing former South African president is being treated, in Pretoria June 28, 2013. REUTERS/Dylan Martinez (SOUTH AFRICA - Tags: POLITICS HEALTH)
ምስል Reuters

ወደፕሪቶርያዉ ሆስፒታል ከገቡ ሶስት ሳምንታትን የያዙት የነፃነት መሪ ኔልሰን ማንዴላ የጤንነታቸዉ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ፤ የአገሪቱ ፕሬዝደንት ጄኮብ ዙማ ወደ ጎረቤት ሀገር ሞዛንቢክ ሊያደርጉት የነበረዉን ጉዞ ሰርዘዋል። ፕሬዝደንት ዙማ በሰጡት መግለጫ፤ ማንዴላ ለሚደረግላቸዉ ህክምና ጥሩ ምላሽን አሳይተዋል ብለዋል። የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዛሬ ማምሻዉን ደቡብ አፍሪቃ እንደሚገቡ ይጠበቃል። የማንዴላ የጤና ሁኔታ፤ ሶስት የአፍሪቃ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ያሉትን የዩናይትድ ስቴትሱን ፕሪዝደንት፤ የደቡብ አፍሪቃ ጉብኝት ሳያደበዝዘዉ እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። በህይወት ዘመናቸዉ ብዙ ዉጣ ዉረድን በፅናት ታግለዉ በድል የተወጡትን የኔልሰን ማንዴላን የጤንነት ሁኔታ ደቡብ አፍሪቃዉያን ብቻ ሳይሆኑ መላዉ ዓለም እየተከታተለ ይገኛል። ማንዴላ በሚቀጥለዉ ወር 95ዓመት ይሆናቸዋል።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ