የስደተኞቹ እልቂት እና የአውሮጳ አስተያየት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2007ማስታወቂያ
ከኢጣልያዊቷ የላምፔዱዛ ደሴት 110 ኪሎ ሜትር ሲቀራት ከሰመጠችው መርከብ እስካሁን 28 ሰዎችን ብቻ ማዳን መቻሉን እና 24 አስከሬኖች ማውጣታቸውን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች አስታውቀዋል። የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ይህ ሁሉ ሰው በደጃፋቸው እየሞተ ርምጃ እንዲወስዱ ጫና አርፎባቸዋል።
ካለፈው ጥር ወር ወዲህ እንኳን ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ናቸው ህይወታቸው ያለፈው። እልቂቱን ምክንያት በማድረግ በወቅቱ የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ሀገር አስተዳደር ሚንስትሮች በሉግዘምቡርግ ስብሰባ ይዘዋል። አውሮጳውያኑ ስለስደተኞቹ እልቂት ምን እያሉ ነው? ቀደም ሲል የብራስልሱን ወኪላችን ገበያው ንጉሤን በስልክ ጠይቄው ነበር።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ