1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች ቀዉስና ስዊድን

ዓርብ፣ ጳጉሜን 6 2007

በብዛት የሚገባዉ ሥደተኛ የሚስተናገድበትን ብልሐት በጋራ ለመፈለግ የሐገሪቱ መንግሥት እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ትናንት ተወያይተዉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።የሐገሪቱ ሕዝብ በፋንታዉ የርዳታ ድርጅቶች ላደረጉለት የድጋፍ ጥሪ አበረታች መልስ እየሰጠ ነዉ

https://p.dw.com/p/1GVEz
ምስል picture-alliance/dpa/B. Nolte

[No title]

እንደ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሐገራት ሁሉ ለስዊድን መንግሥት፤ ለተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ ለርዳታ ድርጅቶችና ለአጠቃላይ ሕዝቡ የስደተኞች ብዛት፤ የማስተናገጃዉ አቅምና ብልሐት አብይ የመነጋገሪያ ርዕሳቸዉ ነዉ። ስዊዲን በርካታ ስደተኞችን በመቀበል ከጀርመን ቀጥሎ ሁለተኛይቱ አዉሮጳዊት ሐገር ናት። በብዛት የሚገባዉ ሥደተኛ የሚስተናገድበትን ብልሐት በጋራ ለመፈለግ የሐገሪቱ መንግሥት እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ትናንት ተወያይተዉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።የሐገሪቱ ሕዝብ በፋንታዉ የርዳታ ድርጅቶች ላደረጉለት የድጋፍ ጥሪ አበረታች መልስ እየሰጠ ነዉ። የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ቴዎድሮስ ምሕረቱ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ