1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች አያያዝ እና የማልቴዘር ጥናት

ሐሙስ፣ መስከረም 18 2010

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያኑ የርዳታ ድርጅት በቅርቡ ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ እንዳስታወቀዉ የስደተኞች ጉዳይ በስሜት ሳይሆን በተረጋጋና በጥሞና መታየት አለበት።

https://p.dw.com/p/2kuVI
Malteser Orden

(Beri.Berlin) Integrationsbericht der Malteser - MP3-Stereo

ጀርመን የገቡ  ስደተኞች ከሕብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለዉ እና ተዋሕደዉ እንዲኖሩ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ማልቴዘር የተባለዉ የርዳታ ድርጅት አሳሰበ።የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያኑ የርዳታ ድርጅት በቅርቡ ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ እንዳስታወቀዉ የስደተኞች ጉዳይ በስሜት ሳይሆን በተረጋጋና በጥሞና መታየት አለበት።ከዚሕ ቀደም በ1950ዎቹና 60ዎቹ ጀርመን የገቡ ስደተኞች ለሐገሪቱ ዕድገት ብዙ መጥቀማቸዉንም ጥናቱ አስታዉሷል።የስደተኞች ጉዳይ ጀርመንን ጨምሮ በብዙ የአዉሮጳ ሐገራት አወዛጋቢ ርዕስ ነዉ።የዶቸ ቬለዉ ማርሴል ፉርስተ ያዘጋጀዉን ዘገባ ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ