1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2005

በተለያዩ የአፍሪቃ እና የአውሮጳ ሀገራት የተካሄደ የእግር ኳስ ውድድር፣ አትሌቲክስ፣ እንዲሁም ፣ የመኪና እሽቅድምድም በዛሬው የስፖርት ክፍለ ጊዜ በሰፊው ይተነተናሉ።

https://p.dw.com/p/19Gnn
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ትናንት ባገኘዉ ድል ፈንጠዝያዉ ቀጥሏል። ከሰባት ሺህ በላይ የሚሆኑ የቡድኑ አድናቂዎች ፍራንክፈርት አዉሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ኖርዌይን አንድ ለባዶ የረታዉን የሴቶች ቡድን ተቀብሏል። በዚህ ዉጤትም ቡድኑ ለስድስተኛ ጊዜ የአዉሮጳ ሴቶች የእግር ኳስ ቡድኖች ሻምፒዮን ሆኗል። የፍጹም ቅጣት ኳሶችን በማዳን ቡድኑን ለድል ያበቃችዉ የጀርመን የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ግብ ጠባቂና አምበል ናዲነ እንገረር ስትሆን በአቀባበሉ የተሰማትን ደስታ በቡድኑ ስም ገልጻለች።

Frauen-EM Finale Deutschland Norwegen Jubel
ድልና ፈንጠዝያምስል picture-alliance/dpa

የቡድኑ አሰልጣኝ ሲልቪያ ናይድ ቡድኑ ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ በተጫዋጮቹ ፈንጠዝያ ታጅበዉ ደስታቸዉን እንዲህ ገልጸዋል፤
«ከመጠን በላይ በጣም ነዉ የተደሰትኩት፤ ሁላችንም እዚህ እንደተመለከትነዉ በእነዚህ ወጣት ሠራዊቶች አማካኝነት ድሉ እንዳሰብነዉ በመሳካቱ ፈንጥዘናል።»
በ49ኛዉ ደቂቃ ነበር አንያ ሚታግ ለቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረችዉ። ጨዋታዉና ድሉ ያጠቃላይ ቡድኑ ድምር ዉጤት ቢሆንም ትናንት አንገረርና ሚታግ በበርካታ ደጋፊዎችና የቡድኑ ተጫዋጮች ሲወደሱ ነበር በስዊድኑ ሶልና ስታዲዮም ያመሹት።

ለዝግጅቱ ሃይማኖት ጥሩነህ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ