1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ምክር ቤት ተደበደበ

ሰኞ፣ ግንቦት 9 2002

36 ተገደሉ። 52 ክፉኛ ቆሰሉ።

https://p.dw.com/p/NQCQ
የአልሸባብ ታጣቂዎችምስል AP

አልሸባብ ግስጋሴው እንደቀጠለ ነው። ሞቃዲሾን በሙሉ ሊቆጣጠራት የቀረው ደካማው መንግስት የሚገኝበት አከባቢ ብቻ ነበር። ትላንት እሁድ የሶማሊያ ምክር ቤት በአልሸባብ የሞርታር ጥይት ሲደበደብ ዋለ። ምክር ቤቱ አንድ ጉዳይ ነበረው--ትላንት። በእርስ በእርስ ጦርነት ለተበጣጠሰችው ሶማሊያ በእርግጥ ፋይዳ ያለው ነገር ያመጣል ብሎ የጠበቀ አልነበረም። የሆኖ ሆኖ ህግ አውጪቹ በምክር ቤቱ ውስጥ እየተነታረኩ እያሉ ከባካራ ገበያ በሚወነጨፉ የሞርታር ጥይቶች ታወኩ። በሶማሊያ መንግስት ወታደሮችና በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሰራዊት የታጠረው ምክር ቤት በእርግጥ አልተጎዳም። በምክር ቤቱ ውስጥ የሚነታረኩት እንደራሴዎችም የደረሰባቸው ጉዳት የለም። በአንጻሩ 26 ንጹሃን በትላንቱ ውጊያ ህይወታቸውን አጥተዋል። 52 ክፉኛ ቆስለዋል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ