1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ሰብዓዊ ቀውስ

ዓርብ፣ ጥቅምት 22 2000

«ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ነው ። በመቅዲሾ ከፊል በተካሄደው ከባድ ውጊያ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ብቻ ዘጠና ሺህ ተጨማሪ ሰዎች ተፈናቅለዋል ። » በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠባባቂ አስተባባሪና የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ተወካይ ክርስቲያን ባልስሌቭ

https://p.dw.com/p/E0Y0
የጎዳና ላይ ውጊያ በሶማሊያ
የጎዳና ላይ ውጊያ በሶማሊያምስል AP

በሰሞኑ የሶማሊያ መዲና መቅዲሾ ውጊያ ምክንያት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ። ድርጅቱ ትናንት ይፋ እንዳደረገው በሰሞኑ ውጊያ የተፈናቀሉት ሶማሊያውያን ቁጥር ሰማንያ ስምንት ሺህ ይደርሳል ። ቀድሞ በተፈናቀለው ላይ የተጨመረውን የአሁኑን ተፈናቃይ ለመርዳት የዕርዳት ድርጅቶች የበኩላቸውን እየጣሩ ነው ። ሆኖም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ የተባበሩት መንግስታትም ሆነ ሌሎች የረድኤት ድርጅቶች የሚገባቸውን ያህል ችግር ላይ ለወደቀው ህዝብ መድረስ አልቻሉም ። ለዚህም የኦቻ ሶማሊያ ሀላፊ ለተፋላሚ ወገኖች ጥሪ አድርገዋል ።