1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት የዕርቅ ጉባዔ

ማክሰኞ፣ ጥር 22 1999

<p>የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ የጎሣና የሃይማኖት መሪዎችን ያቀፈ ሰፊ የዕርቀ-ሰላም ጉባዔ ለመጥራት ተስማሙ።

https://p.dw.com/p/E0Yp
የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ
የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍምስል AP
ይሄው ዕርምጃ የአውሮፓ ሕብረት በሶማሊያ ለሚሰፍር የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ ሃይል ገንዘብ እንዲያቀርብ ጥርጊያ የሚከፍት ሆኖ ታይቷል። የሕብረቱ የልማት ዕርዳታ ኮሜሣር ሉዊስ ሚሼል አዲስ አበባ ውስጥ በአፍሪቃ ሕብረት መሪዎች ጉባዔ አኳያ ከአብዱላሂ ዩሱፍ ከተነጋገሩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሶማሊያው የዕርቅ ጉባዔ በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ሊከፈት እንደሚችል አሰረድተዋል። ሚሼል አያይዘው እንዳሉት የአውሮፓ ሕብረት አሁን ለሰላም ተልዕኮው 19 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። የአፍሪቃ ሕብረት መንግሥታት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል።