1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ችግርና የአፍሪቃ ሕብረት

ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2003

የአፍሪቃ ሕብረት በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የተለያዩ ወገኖች የተለያየ ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ለዉጤት አለመብቃቱን በግልፅ አምኗል።

https://p.dw.com/p/PfIC
የአፍሪቃ ሕብረት ጦር በሞቃዲሾምስል AP

ከዜናዉ እንደ ተከታተላችሁት የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሟል። ይሁንና የአፍሪቃ ሕብረት በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የተለያዩ ወገኖች የተለያየ ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ለዉጤት አለመብቃቱን በግልፅ አምኗል።የሕብረቱ የሠላምና ደሕንነት ምክር ቤት ዛሬ ለምሥራቅ አፍሪቃ፥ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ለአዉሮጳ ሕብረትና ለዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች እንዳስረዳዉ ሶማሊያ በአማፂያንና በመንግሥት ሐይላት ከሚካሄደዉ ዉጊያ በተጨማሪ በመንግሥት ባለሥልጣናት መካካል ያለዉ አለመግባባትም ክፉኛ እየጎዳት ነዉ።

ታደሠ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ