1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ አደጋ፥ ሕገ-መንግሥትና ምርጫ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 25 2004

የአፍሪቃ ሕብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሶማሊያ ጉዳይ ያገባናል ባይ መንግሥታት ባወጡለት እቅድ መሠረት የሽግግር መንግሥቱ ምርጫዉ ከመደረጉ ሕገ-መንግሥት ማስረቅቅና ማፀደቀ አለበት።በጥቃት ግድያዉ መሐል ሕገ-መንግሥት ማርቀቅ፧ ማጸደቅ መቻሉ ብዙ እንዳጠያያቀ ነዉ።

https://p.dw.com/p/14oDg
Soldiers secure the national theatre after an explosion, in Mogadishu April 4, 2012. Al Shabaab rebels in Somalia claimed responsibility for an explosion at the national theatre in Mogadishu on Wednesday that killed at least six people and wounded some government officials. REUTERS/Omar Faruk (SOMALIA - Tags: CIVIL UNREST MILITARY)
ሞቃዲሾዉ የቦምብ ጥቃትምስል Reuters

ሠሜን ሶማሊያ ዱሳማሬብ በተባለች ከተማ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳዉ ቦምብ ሁለት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል።ለጥቃቱ የሶማሊያ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ሐላፊነቱን ወስዷል።በሞቃዲሾ የዶቸ ቬለዉ ዘጋቢ ሁሴን አዌስ እንደሚለዉ የትናንቱ ጥቃት ሶማሊያ ዉስጥ ባለፉት ጥቂት ወራት በተደጋጋሚ ከሚደርሱት ተመሳሳይ አደጋዎች አንዱ ነዉ።አደጋዉ የተባባሰዉ የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት አዲስ ሕገ-መንግሥት ለማፀደቅና ምርጫ ለማድረግ በተዘጋጀበት ወቅት ነዉ።በዚሕም ሰበብ አደጋዉ ሕገ-መንግሥት የማፀደቅና ምርጫ የማድረጉን ሒደት እንዳያጉለዉ አስግቷል።ነጋሽ መሐመድ ጋዜጠኛ ሁሴን አዌስን አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለን።

ዱሳማሬብ ከርዕሠ-ከተማ ሞቃዲሾ አምስት-መቶ ሥልሳ ኪሎ ሜትር ትርቃለች።ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ለጥቂት ቀናት በአሸባብ ታጣቂዎች እጅ ከመዉደቋ በስተቀር፥ ለረጅም ጊዜ የሚቆጣጠራት በኢትዮጵያ ይደገፋል የሚባለዉ እና የሽግግር መንግሥቱ ተባባሪ አሕለል ሱና ወል ጀመዓ የተሰኘዉ ታጣቂ ቡድን ነዉ።

A Somali government soldier patrols the streets of capital Mogadishu February 22, 2012. A London conference on Somalia this week will launch an international "rapid response" fund to help set up schools, hospitals, police and courts in areas recently wrested from the control of Islamist militants. REUTERS/Feisal Omar (SOMALIA - Tags: SOCIETY CIVIL UNREST POLITICS MILITARY)
ምስል Reuters

ትናንት ግን አሸባብ እንደገና አጠቃባት።አክራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ባለፈዉ መጋቢት ማብቂያ ሞቃዲሾ ቲያትር ላይ እንዳደረገዉ ሁሉ የሚገድል-የሚያቆስል ወይም የሚያሸብረዉን ወገን በቅጡ ለይቶ የሚያዉቅ ነዉ የሚመስለዉ።ባለሥልጣናትን።
ቡድኑ እንዳዘመተዉ ያስታወቀዉ አጥፍቶ ጠፊ የታጠቀዉን ቦምብ ያፈነዳዉ ከሞቃዲሾ የሔዱ የምክር ቤት እንደራሴዎች ካረፉበት ሆቴል ነበር።

«ከአካባቢዉ በደረሰን የመጀመሪያ ዘገባ መሠረት በአደጋዉ ስምንት ሰዎች ሞተዋል።ቢያንስ ሁለቱ የምክር ቤት አባላት ነበሩ።ከሞቱት በተጨማሪ ሃያ-ያሕል ሰዎች ቆስለዋል።ከቁስለኞቹ የተወሰኑት ለሕክምና ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል።»
የትናንቱ ጥቃት አምስተኛ ወሩን በያዘዉ የጎሮጎሮሳዉያኑ ሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት ዓመት በተለያዩ ከተሞች በተደጋጋሚ ከደረሱና ከሚደርሱት አደጋዎች አንዱ ነዉ።ጋዜጠኛ ሁሴይን በየሥፍራዉ ማዕለት፥ወሌት የሚደርሰዉን የቦምብ ጥይት ጥቃት፥ግድያ ድግግሞሽ ለመግለፅ «በጣም» የሚለዉን ቃል አንዴ ማለቱ አልበቃዉም።ሰባቴ ደገመዉ፥

«ሁኔታዉ አሁን በጣም፥ በጣም፥ በጣም አደገኛ እየሆነ ነዉ።ምክንያቱም ፍንዳዉ፥ ተኩሱ፥ ግድያዉ ቀን ከሌት በጣም፥ በጣም፥ በጣም፥ በጣም እየጨመረ ነዉ።»ያም ሆኖ የጋሮዉ ስምምነት ተብሎ በሚጠራዉ ዉል መሠረት ለበርካታ ዓመታት ሲገፋ፥ ሲሸጋሸግ የቆየዉ ምርጫ የፊታችን ነሐሴ ይደረጋል።የአፍሪቃ ሕብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሶማሊያ ጉዳይ ያገባናል ባይ መንግሥታት ባወጡለት እቅድ መሠረት የሽግግር መንግሥቱ ምርጫዉ ከመደረጉ ሕገ-መንግሥት ማስረቅቅና ማፀደቀ አለበት።
በጥቃት ግድያዉ መሐል ሕገ-መንግሥት በተገቢዉ መንገድ ማርቀቅ፧ ማጸደቅ መቻሉ ብዙ እንዳጠያያቀ ነዉ።የሽግግር መንግሥቱ ሰሞኑን እንዳስታወቀዉ ግን ዕቅዱ እንደተጠበቀ ነዉ።እንደገና ጋዜጠኛ ሁሴይን፥-

«መንግሥት እንደሚለዉ ረቂቅ ሕገ-መንግሥቱ በያዝነዉ ወር (ግንቦት) ይፀድቃል።በሌላ በኩል ግን ተቃዋሚዎች ሕገ-መንግሥት የማርቀቅና የማፅደቁን ሒደት ለማወክ በተደጋጋሚ አደጋ እንደሚጥሉ እየዛቱ ነዉ።»
ሕገ-መንግሥት የማፅደቁ ሒደት ከአሸባብ፥ ወይም ከሌሎች ታጣቂ ተቃዋሚ ሐይላት ብቻ ሳይሆን በራሱ በሽግግር መንግሥቱ ካሉ ወገኖችም ተቃዉሞ ገጥሞታል።እነዚሕም ወገኖች ሕዝቡ ረቂቅ ሕገ-መንግሥቱን እንዳይቀበለዉ እየቀሰቀሱ ነዉ።ምክንያት፥-ሁሴይን ይነግረናል።

«እነሱ እንደሚሉት ይሕ ረቂቅ ሕገ-መንግሥት እስላማዊዉን አስተምሕሮት የሚፃረር ነዉ።ሥለዚሕ ሕዝቡ ረቂቁቁን መቀበል የለበትም እያሉ ሕዝቡ እንዳይቀበለዉና እንዳይፀድቀዉ እየነገሩት ነዉ።»
ሶማሊያ። ዩጋንዳ ዉስጥ የአሜሪካ ባሕር ወለድ ወታደሮች የሚዘምትባትን የዩጋንዳ ጦር ያሰለጥኑላታል። ፈረንሳይ ዉስጥ ዕሁድ በሚደረገዉ ምርጫ ፕሬዝዳት ኒካላ ሳርኮዚን የሚፎካከሩት፥ የፍራንሷ ኦላንድ ባለቤት የቀዳሚ እመቤትነቱን ደረጃ ካገኙ አስቀድመዉ ሊጎበኟቸዉ ከሚፈልጓቸዉ አምስት ሐገራት አንዷ-ያቺ ሐገር ናት።ሶማሊያ።

ነጋሽ መሐመድ

NUR ZUR REDAKTIONELLEN NUTZUNG! A handout picture provided by the African Union-United Nations Information Support Team shows a Ugandan soldier serving with the African Union Mission in Somalia (AMISOM) standing at the back of an amoured fighting vehicle near a defensive position along the front-line in the Yaaqshiid District of northern Mogadishu, Somalia, 05 December 2011. In the face of a surge of car bombings and improvised explosive device (IED) attacks, the 9,700-strong African Union force continues to conduct security and counter-IED operations in and around the Somali capital. EPA/STUART PRICE / AU-UN IST PHOTO / HANDOUT HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++ dpa 28561906
የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊትምስል picture-alliance/dpa

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ