1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ዓለም ዓቀፍ አገናኝ ቡድን ስብሰባ በሮም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001

በኢጣልያ አስተናጋጅነት ዛሬ በርዕሰ ከተማይቱ በሮም የሶማሊያ ዓለም ዓቀፍ አገናኝ ቡድን ዝግ ጉባኤ ተጀምሯል ።

https://p.dw.com/p/I6Oo
ምስል AP

የሶማሊያ ተፋላሚ ወገኖችን ለማቀራረብና ሀገሪቱን ለማረጋጋት ጥረት በሚያደርገው የአገናኝ ቡድኑ የሁለት ቀናት ጉባኤ ላይ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ሻርማርኬ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዱላሂ ኦማር ተካፋይ ሲሆኑ ከኢጣልያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንኮ ፍራቲኒ ተገኝተዋል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶማሊያ ልዩ ልኡክ ኡልድ አብደላ እንዲሁም የአርባ አገራት እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በዚሁ ጉባኤ ላይ ተካፋይ መሆናቸውን የኢጣልያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን መግለጫ ጠቅሶ ተክለ እግዚ ገብረ የሱስ ዘግቧል ።

ተክለእዝጊ ገብረየሱስ/ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ