1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎችና የአዉሮጳ ሕብረት

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001

የአዉሮጳ ሕብረት የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎችን እንዲወጋ ያዘመተዉን ባሕር ወለድ ጦር ለማጠናከር ሚንስትሮቹ ሲወስኑ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥትን ለመደገፍም በድጋሚ ቃል ገብተዋል

https://p.dw.com/p/HuIt
የባሕር ወንበዴዎቹ አርማምስል picture alliance / dpa

የኢጋድ አባል ሐገራት ሚንስትሮች ሥለ ሶማሊያ ቀዉስ ለመምከር ዛሬ አዲስ አበባ ከመሰብሰባቸዉ በፊት ባለፈዉ ሰኞ የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮች ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ተሰብስበዉ ሥለሶማሊያ ሁኔታ ተነጋግረዉ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎችን እንዲወጋ ያዘመተዉን ባሕር ወለድ ጦር ለማጠናከር ሚንስትሮቹ ሲወስኑ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥትን ለመደገፍም በድጋሚ ቃል ገብተዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ/ነጋሽ መሐመድ/ሂሩት መለሰ