1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን መልቀቅ

ሰኞ፣ ሰኔ 13 2003

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ አብዱላሂ አህመድ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ትናንት አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/RUkv
ምስል DW

አብዱላሂ ትናንት እንደተናገሩት ከስራ ለመሰናበት የወሰኑት ለሶማሊያውያን ጥቅም ሲሉ እና የሶማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን የወረዱት የሶማሊያው ፕሬዝዳንትና የሶማሊያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ካምፓላ ውስጥ በተካሄደ ድርድር በሃገሪቱ ምርጫ የሚካሄድበትን ጊዜ ለማረዘም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኃላ ነው ። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድና የፓርላማው አፈ ጉባኤ ሸሪፍ ሀሰን ሼክ አደን የሶማሊያውን ምርጫ ለማራዘም ካምፓላ ኡጋንዳ ውስጥ ስምምነት ላይ የደረሱት ባለፈው ሐሙስ ነበር ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ