1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ውሳኔዎች

ዓርብ፣ ግንቦት 14 2012

ምክር ቤቱ የተወሰኑ አባላቱ ቢወጡም ስብሰባውን ለማስቀጠል በቂ አባላት በመቅረታቸው ስብሰባውን ቀጥሎ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ወ/ሮ ሂቦ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ዶ/ር ኒምዓን አብዱላሂ በምንም መልኩ ስብሰባውን ለማስቀጠል የሚያስችል አባል አልቀረም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3cdhv
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

          
የሶማሌ ክልል ም/ቤት ትናንት ዛሬ ባካሄደው ጉባዔ አስረኛ መደበኛ ጉባዔ ጉባዔውን ረግጠው ወተዋል ያላቸውን አስራ ሁለት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ሲያነሳ የአራት ሰዎችን ሹመት አፅድቋል።  በትላንትናው ዕለት ሲጀመር ከመነሻው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ተበትኗል ሲባል የነበረው የሶማሌ ክልል ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ የተወሰኑ አባላቱ ረግጠው ሲወጡ በተቀሩት አባላት ስብሰባውን አካሂዷል። የምክር ቤቱ አባል የሆኑት እና ስብሰባውን ረግጠው ከወጡት አንዱ ዶ/ር ኒዒማን አብዱላዒ ለDW በስልክ በሰጡት ማብራርያ ስብሰባውን ለቀው የወጡበትን ምክንያት አስረድተዋል ።ምክር ቤቱ የተወሰኑ አባላቱ ቢወጡም ስብሰባውን ለማስቀጠል በቂ አባላት በመቅረታቸው ስብሰባውን ቀጥሎ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ወ/ሮ ሂቦ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ኒምዓን አብዱላሂ በምንም መልኩ ስብሰባውን ለማስቀጠል የሚያስችል አባል አልቀረም ብለዋል።
የምክር ቤቱ አባል ባይሆኑም በስብሰባው ላይ ተገኝተው እንደነበር የገለፁት የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሂቦ መሀመድ ለDW በስልክ በሰጡት ማብራርያ የምክር ቤቱ አጀንዳ ሲቀርብ ሁከት መነሳቱን ጠቁመዋል ። በዚህም ስብሰባውን ረግጠው የወጡ አባላት መኖራቸውንና ነገር ግን ስብሰባውን ለማስቀጠል የሚያስችል አባል በመኖሩ ስብሰባው መቀጠሉን አስረድተዋል ።
ወ/ሮ ሂቦ የምክር ቤቱ ስብሰባ ሲቀጥል የምክር ቤቱ ህግ አውጪ ኮሚቴ ከም/ቤቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡ አካላትን በሚመለከት ባቀረበው ጥያቄ አጀንዳ መያዙንና በዚህም የአስራ ሁለት አባላት ያለመከሰስ መብት ሲነሳ ሌሎች ውሳኔዎችም ተወስነዋል ብለዋል።ስብሰባውን ረግጠው የወጡ አባላት የምክር ቤቱ አፈጉባዔ አለ አግባብ ተነስተዋል ከሚል በተጨማሪ አስፈፃሚው በርካታ ችግሮች ያሉበት እና እምነት የሚጣልበት ባለመሆኑ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት የመተማመኛ ድምፅ እንዲሰጥ ጥያቄ ማቅረባቸውን ቢገልፁም ወ/ሮ ሂቦ እንዲህ ያለ ነገር አለመነሳቱን ተናግረዋል።ለምክር ቤቱ ጥያቄ አቅርበው ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል የተባሉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ በሌላ ኃላፊነት ሲሾሙ በምትካቸው ምንም ዓይነት ሹመት አለመካሄዱ ታውቋል።

መሳይ ተክሉ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ