1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያ ተቀናቃኝ ወገኖች ስምምነት

ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2000

የሶማልያ ተቀናቃኝ ወገኖች ስምምነት በጅቡቲ ካለፈው ሣምንት ወዲህ በተመድ አስተባባሪነት የተወያዩት የሶማልያ ሽግግር መንግሥትና የተቃውሞው ኅብረት ለሶማልያ ዳግም ነጻነት ተወካዮች ትናንት አንድ ስምምነት ደረሱ።

https://p.dw.com/p/EHb4
የቀጠለው ሁከት ሰለባ የሆነ አንድ ሲቭል የሶማልያ ተወላጅ
የቀጠለው ሁከት ሰለባ የሆነ አንድ ሲቭል የሶማልያ ተወላጅምስል AP

በስምምነቱ መሠረት፡ ሁለቱ ወገኖች በሚቀጥለው ወር ሦስት ወር የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ደምብ ይደርሳሉ። ይሁንና፡ አስመራ የሚገኙት አንዳንድ የሶማልያ ዳግም ነጻነት ቡድኖች የጅቡቲውን ስምምነት እንደማይቀበሉ ከወዲሁ ካስታወቁ በማስታወቃቸው፡ ስምምነቱ መሳካቱ አጠራጣሪ ሆኖዋል።