1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያ የጸጥታ ሁኔታ

ረቡዕ፣ መጋቢት 19 1999

ባለፈዉ ሳምንት በሶማልያ መዲና መቅዲሾ ዉስጥ በኢትዮጽያ በሚታገዙ የሶማልያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች ላይ ከደረሰዉ ከባድ ጥቃት በኻላ በከተማይቷ በጥቂቱ መረጋጋት ይታያል

https://p.dw.com/p/E0Yb
በመቅዲሾ ከባድ ግጭት
በመቅዲሾ ከባድ ግጭትምስል picture-alliance/dpa

በዚሁ ከባድ ግጭት ምክንያት ከተማዋን ለቀዉ የነበሩ ነዋሪዎች በመመለስ ላይ መሆናቸዉ የአይን ምስክሮች ይገልጻሉ። በሌላ ዜና በመቅዲሾ አንድ አጥፍቶ ጠፊ እራሱን ማንጎዱ ተዘግቦአል። በሶማልያ ያለዉን ወቅታዊ ሁኔታ በመቅዲሾ ነዋሪ የሆነዉን የአዣንስ ፍራንስ ፕሪስ ዘጋቢ ሙስጠፋ አብዲኑርን አዜብ ታደሰ አነጋግራዋለች

በመቅዲሾ ከተከሰተዉ ከባድ ጥቃት ወዲህ ከተማዋ ለአራት ቀናት በዉጥረት ቆይታ በትናንትናዉ እለት በመቅዲሾ መንገዶች ነዋሪዎችዋ ታይተዋል። ይህንኑ ዉጥረት በመሸሽ ከተማዋን ለቀዉ የነበሩ ወደ የቤቶቻቸዉ እየተመለሱ መሆኑም ታዉቋል። ሻቤለ ኔት የተባልለዉ ድረ-ገጽ የከተማዋን ነዋሪ ስም ጠቅሶ እንደዘገበዉ የብዙሃን መገናኛዎች «የተነሳዉ የተኩስ ልዉዉጥ ቆሞአል» የሚለዉን ዜና ከተሰራጨ ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ የቤታቸዉ እንደተመለሱ ገልጾአል። በሶማልያ የሚገኘዉ የአዣንስ ፍራንስ ፍሪስ ዘጋቢ መቅዲሾ ከምንግዜዉም በላይ ተራጋግዛለች ባይ ነዉ

«በእዉነቱ ዛሪ ከተማይቱ የተረጋጋች ትመስለላለች ምንም አይነት ግጭት ወይም ተኩስ አይታይም። ትናንትና ማታ ዛሪ ጠዋትም ቢሆን ምንም አይነት ተኩስ አልተሰማም። በአኢትዮጽያ የጦር መኮንንች እና የሃዉያ የጎሳ መሪዎች መካከል የተኩስ አቁሙ ድርድር ተካሂዶአል ተብሎአል። በጉዳዩ ተስማምተዋል። በዚህም ምክንያት ምንም አይነት ግጭት እና ብጥብጥ አይታይም»

Daryeel Bulsho Guud በሶማልያ ቋንቋ ምህጻረ ቃሉ DGB ተብሎ የሚታወቀዉ የእርዳታ ድርጅት ከጀርመን ያገኘዉን መድሃኒት እርዳታ መቅዲሾ ለሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ማከፋፈሉ ታዉቋል። መድሃኒቱ በተለይም በወቅቱ በአሪገቷ የተነሳዉን የተቅማጥ ወረርሽኝ ለመግታት የታሰበ ነዉ። በሌላ ዜና ከትናንት በስትያ የኢትዮጽያ ወታደሮች በሰፈሩበት ካንፕ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በያዘዉ መኪና ላይ ያጠመደዉን ቦንብ ማፈንዳቱን የዣንስ ፍራንስ ፕሪስ ዘግቦአል። ፍንዳታዉ የደረሰዉ በሰሜናዊ መቅዲሾ አቅራብያ በሰፈሩት የኢትዮጽያ ጦር ሰራዊት ካንፕ ደጃፍ ላይ ነዉ፥ ይላል ሙስጠፋ አብዲ
«አጥፍቶ ጠፊዉ ራሱን ያነጎደዉ በሚነዳዉ መኪናዉ ዉስጥ ባጠነደዉ ቦንብ ነዉ። የኢትዮጽያ ወታደሮች በሰፈሩበት ካንፕ ነድቶ መግባት ነበር የፈለገዉ። ነገር ግን ከግንብ ተጋጭቶ እራሱን አንጉዶአል። በዚህ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ወታደሮች ቆስለዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጽያ ወታደሮች ጥቃቱን ለመከላከል ባነሱት ተኩስ አንድ የታክሲ ሹፊር ተገድሎአል»

ይህ ቦንብ በፈንዳበት በዝያዉ አካባቢ ከትናንት በስትያ ለሊት ሌላ አንድ መኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ መፈንዳቱ ተዘግቦአል። ነገር ግን በፍንዳታዉ አንድም የተጎዳ አልነበረም። በሶማልያ ሰላም ለማስፈን ይገባል ተብሎ ከታቀደዉ ስምንት ሽህ የአፍሪቃ ህብረት ጦር መካከል ከኡጋንዳዉ ጦር ሰራዊት ቀጥሎ የቡሩንዲዉ ጦር በቅርቡ እንደሚገባ የጦሩ ቃል አቀባይ ዛሪ ገልጸዋል። ብሩንዲ በአፍሪቃዉ ህብረት ጦር ስር 1700 ያህል ወታደሮች እንደምታሰፍር ቃል መግባትዋ ይታወሳል። የአፍሪቃዉ ህብረት በሶማልያ ሊያዘምት ከአቀደዉ ስምንት ሺህ ጦር ሰራዊት መካከል በአሁኑ ወቅት 1200 ያህል የኡጋንዳ ወታደሮች በመቅዲሾ ሰፍረዉ ይገኛሉ።