1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶሪያዊዉ ስደተኛ ጉዞው

ዓርብ፣ ሰኔ 12 2007

ሶሪያዊው አህመድ በሜዲቴራንያን ባህር ተጉዞ በሁለተኛ ሙከራ ተሳክቶለት አውሮፓ ገብቷል ። የዛሬ ሁለት ዓመት ከቀዮው የተሰደደው አህመድ የአውሮፓን ምድር ለመርገጥ አንድ ዓመት ጀርመን ለመግባት ደግሞ ሌላ አንድ ዓመት ወስዶበታል ። ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ

https://p.dw.com/p/1FjtV
Flüchtlinge Grenzgebiet Türkei Syrien
ምስል Getty Images/AFP/B. Kilic

[No title]



የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ UNHCR እንዳስታወቀው በጎርጎሮሳዊው 2014 መጨረሻ ላይ በዓለማችን ግጭቶችንና ሞትን በመሸሽ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 60 ሚሊዮን ደርሷል ። በአሁኑ ጊዜ በቱርክ ብቻ 1 ሚሊዮን 700 ሺህ የሶሪያ ስደተኞች ይገኛሉ ። በአደገኛ የባህር ላይ ጉዞ ወደ አውሮፓ ከሚሰደዱት መካከል ሶሪያውያን በቁጥር ብዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ ።ከሊቢያ ከሚነሱት ሶሪያውያን ስደተኞች የቀናቸው አውሮፓ ሲደርሱ አንዳንዶች ደግሞ ተይዘው ወደ መጡበት ሊመለሱ መንገድ ላይ ህይወታቸውም ሊያልፍም ይችላል ። ዶቼቬለ ያነጋገረው ሶሪያዊው አህመድ በሜዲቴራንያን ባህር ተጉዞ በሁለተኛ ሙከራ ተሳክቶለት አውሮፓ ገብቷል ። የዛሬ ሁለት ዓመት ከቀዮው የተሰደደው አህመድ የአውሮፓን ምድር ለመርገጥ አንድ ዓመት ጀርመን ለመግባት ደግሞ ሌላ አንድ ዓመት ወስዶበታል ። የዶቼቤለ የካይሮ ዘጋቢ Sabine Rossi ስለ አህመድ የስደት ጉዞ የዘገበችውን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ