1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶርያ ወቅታዊ ሁኔታ

ሰኞ፣ ሐምሌ 11 2003

ሶሪያ ውስጥ በአምባገነኑ ገዢ በፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ በዋና ከተማይቱ በዳማስቆስ ጭምር እየጠነከረ ነው። የአገሪቱ የመብት ተቆርቋሪዎች እንዳስታወቁት ባለፈዉ አርብ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ሲወጡ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋርም በየቦታው ግጭት ደርሶ ነበር።

https://p.dw.com/p/RaUd
የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች በኢስታምቡሉ ስብሰባምስል Picture-Alliance/dpa

የሶሪያ ተቃዋሚ ወገን የፖሊሱን የሃይል ዕርምጃ ምክንያት በማድረግ ዳማስቆስ ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ በነበረ "አገር አድን" ጉባዔ ላለመሳተፍ መወሰናቸዉ አይዘነጋም። በሌላ በኩል በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች የአሣድን አገዛዝ በጋራ ለመጣል የሚያስችል ስልት ለመወጠን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቱርክ ውስጥ ተሰብስበዉ ነበር። ይሄው የኢስታምቡሉ ስብሰባ የሶሪያ ተቃውሞ ባለፈው መጋቢት ወር ከጀመረ ወዲህ በዓይነቱ ከአገሪቱ ውጭ ታላቁ መሆኑ ነው። የሶርያን ወቅታዊ ሁኔታ ነብዪ ሲራክ ከሳዉዲአረብያ ዘገባ ልኮልናል።

ነብዪ ሲራክ

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ