1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሺሞን ፔሬስ ህልፈተ ሕይወት

ረቡዕ፣ መስከረም 18 2009

የቀድሞው የእስራኤል ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ አረፉ። የ93 ዓመቱ ታዋቂ ፖለቲከኛ ከሁለት ሳምንታት በፊት ደም ጭንቅላታቸው ውስጥ ከፈሰሰ በኋላ ሀኪም ቤት መግባታቸው የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/2Qhf0
USA Schimon Peres in Washington
ምስል Reuters/B. McDermid

mmt Q & A(zum Tod von Schimon Peres) - MP3-Stereo

እጎአ ከ2007 እስከ 2014 ዓም ፕሬዚደንት የነበሩት የሰራተኛው ፓርቲ መሪ ፔሬስ ሁለት ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። እስራኤል እና የእስራኤል ሕዝብ፤ የእስራኤል መስራች አባት በሚባሉት በቀድሞው ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ ሞት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል። የተለያዩ የውጭ ሀገራት መሪዎችም የሀዘን መግለጫቻውን ለእስራኤል መንግ/ስት እና ሕዝብ በመላክ ላይ ናቸው።  ሺሞን ፔሬስ እጎአ በ1994 ዓም ከቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ይትዝሀቅ ራቢን እና የቀድሞው የፍልስጤማውያን መሪ ያሲር አራፋት ጋር ባንድነት በፍልስጤማውያን እና በእስራኤል መካከል በኦስሎ፣ ኖርዌይ ለደረሱት የሰላም ስምምነት የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ሆነዋል።  

ዜናነህ መኮንን

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ