1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብር ስጋት በኢጣልያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 9 2008

በኢጣልያ በተለይ ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ የፀጥታ ጥበቃው ተጠናክሮ ከፍተኛው ደረጃ ደረሶዋል። አሸባሪዎች በመላ ኢጣልያ ጥቃት ሊጥሉ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ የፀጥታ ኃይላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ተደርጎዋል።

https://p.dw.com/p/1Jidk
Italien Anti-Terror-Einheit GIS Militärparade
ምስል Getty Images/AFP/A. Solaro

[No title]

በሀገር አስተዳደሩ ሚንስትር አንጀሊኖ አልፋኖ ትዕዛዝ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ከሀገሪቱ የማባረሩ ተግባር ተጠናክሮዋል። ባለፈው ቅዳሜ እንኳን በፒዛ ገዳዳ ሀውልት ላይ ጥቃት አቅደዋል በሚል የተጠረጠሩ በፑሊያ ፣ አንድሪያ የሚገኝ የአንድ መስጊድ ኢማም የሆኑ አንድ ቱኒዝያዊ ዋ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አዘዋል። ካለፈው ዓመት ወዲህ የሀገር አስተዳደሩ ሚንስትር አንጀሊኖ አልፋኖ 109 ተጠርጣሪዎችን የማባረር ትዕዛዝ የፈረሙ ሲሆን፣ 43 ን እጎአ በ2016 ነው የፈረሙዋቸው። በኢጣልያ ስለተጠናከረው የሽብርተኝነት ስጋት እና የፀጥታ ጥበቃ ርምጃ ሮም የሚገኘውን ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ተኽለእግዚ ገብረየሱስ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ