1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብር ተጠርጣሪዎች ክስ-የጋዜጠኛዉ ስደት

ረቡዕ፣ ኅዳር 13 2004

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ-ሕግን ማብራሪያና የተከሳሽ ጠበቆችን ተቃዉሞ አድምጧል።ችሎቱ የተከሳሽ ጠበቆች ባቀረቡት ተቃዉሞ ብይን ለመስጠት ለነገ-ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል-----ጋዜጠኛ ዳዊት የ1997ቱ ምርጫ አወዛጋቢ ዉጤት በጫረዉ ግጭት ሰበብ ተበይኖበት የነበረዉ የአራት አመት እስራት በይቅርታ ነበር የተነሳለት

https://p.dw.com/p/Ry7z


የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ጥርጣሬ ያሰራቸዉ ሃያ-አራት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ዛሬም በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።አዲስ አበባ ያስቻለዉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰወስተኛ ወንጀል ችሎት የመሐል ዳኛ በተጠርጣሪዎች ላይ የተመሠረተዉን ክስ በንብባ አሰምተዋል።ክሱ ከተሰማ በሕዋላ ፍርድ ቤቱ የአቃቤ-ሕግን ማብራሪያና የተከሳሽ ጠበቆችን ተቃዉሞ አድምጧል።ችሎቱ የተከሳሽ ጠበቆች ባቀረቡት ተቃዉሞ ብይን ለመስጠት ለነገ-ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።------------

የዳዊት ከበደ ስድት

በሌላ በኩል ሠሞኑን ከኢትዮጵያ የተሰደደዉ የአዉራምባ ታይምስ የአስተዳዳር አርታኤ ዳዊት ከበደ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚሕ ቀደም ያደረገለትን ይቅርታ ገፍፎ ዳግም ሊያስረዉ መዘጋጀቱን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ አለኝ አለ።ዳዊት ዛሬ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረገዉ ቃለ-ምልልስ እንዳለዉ ዳግም ሊታሰር እንደነበረ የሰማዉ የተደረገለት ይቅርታ እንዲነሳ በመከረዉ የመንግሥት ባለሥልጣት ስብሰባ ላይ ከተካፈለ ሰዉ ነዉ።ጋዜጠኛ ዳዊት የ1997ቱ ምርጫ አወዛጋቢ ዉጤት በጫረዉ ግጭት ሰበብ ተበይኖበት የነበረዉ የአራት አመት እስራት በይቅርታ ነበር የተነሳለት።ተክሌ የኋላ ዳዊት ከበደን በስልክ አነጋግሮታል።

LOGO CPJ

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ