1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር

ሰኞ፣ መስከረም 10 2008

ተገልጋዮቹ አነስተኛ ያሏቸው አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉም ጠይቀዋል ።ባቡሩ ሥራ መጀመሩ የከተማይቱን የማጓጓዣ እጥረት ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ።

https://p.dw.com/p/1GZzS
Äthiopien U- und Straßenbahn in Addis Abeba
ምስል DW/J. Gebreegziabher

[No title]



የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ከትናንት ጀምሮ በአንድ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ። በዚሁ ከቃሊቲ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ አደባባይ በሚዘልቀው መስመር በተጀመረው አገልግሎት መደሰታቸውን ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አብዛኛዎቹ ተጓዦች ተናግረዋል ። ሆኖም ተገልጋዮቹ አነስተኛ ያሏቸው አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉም ጠይቀዋል ።ባቡሩ ሥራ መጀመሩ የከተማይቱን የማጓጓዣ እጥረት ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። የባቡር ተጓዞችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ