1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀላል የጦር መሣሪያ ዝውውር እና የደቀነው አሳሳቢ ችግር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 1997

አሁኑ ጊዜ በብዙ የዓለም ሀገሮች ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚዘዋወረው የጦር መሣሪያ፡ በተለይም ቀላሎቹ የጦር መሣሪያ መጠን እየተበራከተ መሄዱን አንድ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ተሟጋች ድርጅት የተሰኘ ዓለም አቀፍ ፀረ ጦር መሣሪያ ቡድን ገለፀ።

https://p.dw.com/p/E0k2

የዚሁ ብዙ ጥፋት አድራሹ የጦር መሣሪያ ዝውውር፡ በተለይ አፍሪቃ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ ያስታወቀው ይኸው ቡድን ባለፈው የሣምንት መጨረሻ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ቀላሉ የጦር መሣሪያ የደቀነውን ከፍተኛ ችግር ሊቀነስ ወይም ከተቻለ በጠቅላላ ሊወገድ ስለሚችልበት ጉዳይ ከሌሎች ተመሳሳይ ዓለም አቀፍና ያካባቢ ድርጅቶች ጋር መክሮዋል።