1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀኝ አክራሪዎች እንቅስቃሴ በጀርመን

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2004

እጎአከ 2000 እስከ 2007 በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች ፣ 9 የውጭ ዜጎችና የአንድ የጀርመን ፖሊስ በህቡዕ በሚንቀሳቀስ የቀኝ ፅንፈኞች ቡድን ሳይገደሉ እንዳልቀረ ይፋ ከሆነ በኋላ ግድያውንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተሰይሞ ምርመራው ቀጥሏል ። በመካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው

https://p.dw.com/p/15hMI
Teilnehmer der NPD-Veranstaltung «Rock für Deutschland» warten am Samstag (11.07.2009) in Gera auf Einlaß in einen abgesperrten Park. Zeitgleich protestieren mehrere hundert Menschen mit einer Kundgebung und einem Demonstrationszug gegen dieses Konzert. Die Veranstaltungen werden von einem Großaufgebot von Polizeieinheiten aus mehreren Bundesländern abgesichert. Foto: Peter Müller dpa/lth (zu dpa 4178 und lth 4172 vom 11.07.2009) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

እጎአከ 2000 እስከ 2007 በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች  ፣ 9 የውጭ ዜጎችና የአንድ የጀርመን ፖሊስ በህቡዕ በሚንቀሳቀስ የቀኝ ፅንፈኞች ቡድን ሳይገደሉ እንዳልቀረ ይፋ ከሆነ በኋላ ግድያውንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተሰይሞ ምርመራው ቀጥሏል ። በመካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የጀርመን የሃገር ውስጥ ስለላ መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊና ሌሎችም ባለሥልጣናት ሥራቸውን ለቀዋል ። መስሪያ ቤቱምበቅርቡ አዲስ ሃላፊ ተሾሞለታል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በጀርመን የቀኝ ፅንፈኞች እንቅስቃሴልዩ ልዩ ገፅታዎች ላይ ያተኩራል ።                                          

ከዛሬ 12 አመት አንስቶ እጎአ እስከ 2007 ዓም ድረስ 9 የውጭ ተወላጆችና አንድ ጀርመናዊ ፖሊስ በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች በነማን እንደተገደሉ እስካለፈው ህዳር ድረስ ሳይታወቅ መቆየቱ እስካሁን አነጋግሮ ያላበቃ ጉዳይ ነው ። ግድያውን ፈፅመዋል የተባሉትን በህቡዕ የሚንቀሳቀሰው የብሔራዊ ሶሻሊስት ቡድን አባላት የጀርመን የሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት በቅርብ አለመከታተሉና በነርሱም ላይ እርምጃ ያለ መውሰዱ ምክንያት 11 አባላት ባሉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴ እየተጣራ ነው ። የቱርኩ ተወላጅ አበባ ነጋዴው Envore Simsek በህቡዕ በሚንቀሳቀሰው በአሸባሪው ብሔራዊ ሶሻሊስት ቡድን እጎአ በ 2 ሺህ ኑርበርግ ውስጥ ተተኩሶበት የተገደለ የመጀመሪያው ሰለባ ነበር ። 

ARCHIV - Die BKA-Handouts vom 01.12.2011 zeigen Uwe Böhnhardt (l-r), Uwe Mundlos und Beate Zschäpe (Fotos von 2007,2009 und 2011; Bildkombo). Die Bundesanwaltschaft hat am Mittwoch (25.01.2012) bundesweit Wohnungen und Geschäftslokale von mutmaßlichen Unterstützern der Zwickauer Neonazi-Terrorzelle durchsucht. Wie die Behörde am Mittwoch in Karlsruhe mitteilte, sollen die Beschuldigten den mutmaßlichen Terroristen der Vereinigung «Nationalsozialistischer Untergrund» (NSU) Schusswaffen und Sprengstoff verschafft haben. Es seien Wohnungen und Geschäfte in Sachsen, Thüringen und Baden-Württemberg durchsucht worden. BKA/ dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

ከዚያም ቡድኑ በቀጠሉት አመታት 7 የቱርክ እንዲሁም አንድ የግሪክ ዜጋ በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ውስጥ ገድሏል ።  የዚህ ተከታታይ ግድያ የመጨረሻዋና 10 ኛ ሰለባ እጎአ ሃይልብሮን ውስጥ የተገደሉት ጀርመናዊቷ ሴት ፖሊስ ሚሼል ኪዘቬተር ናቸው ። ከነዚህ ግድያዎች በስተጀርባ በውጭ ዜጎች ጥላቻ የተሞሉት 3 ቱ  Beate Zschäpe ፣ Uwe Mundlosና Uwe Böhnhardt እንዳሉበት በአጋጣሚ የታወቀው ከ 12 አመት በኋላ  በዚህ ዓመት በህዳር ወር ነበር ። የጀርመን ፖለቲከኞችና ህዝቡ የጀርመን የሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት የቡድኑ አባላት ከዓይኑ ስር ሆነው  10 ሰዎች ሲገድሉ እንዴት ላይታወቁ ቻሉ የሚለውን ጥያቄ ደጋግመው ማንሳታቸውን ቀጥለዋል ። የደህንነት ሠራተኞች 10 ን ሰዎች ማን እንደገደላቸው ለማወቅ ይህን ያህል ጊዜ መውሰዳቸው አስደንጋጭ ሆኖ ነው የተገኘው ። እስካሁን መልስ ያላገኙ የተለያዩ ጥያቄዎች በተነሳበት በዚህ ተከታታይ ግድያ ሰበብ ለረዥም ጊዜ የፌደራል ጀርመን የሃገር ውስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊ የነበሩት Heinz Fromm እድሜያቸው ሳይደርስ ጡረታ ለመውጣት ተገደዋል ። ከነገ ጀምሮም በFromm ቦታ Hanns Georg Maassen ይተካሉ ። Maassen በጀርመን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሸባሪዎች ጉዳይ አጥኚ ናቸው ። አዲሱ ተሿሚ ለተሰጣቸው ሃላፊነት ብቁ እንደሆኑ የጀርመን የሃር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሃንስ ፔተር ፍሬድሪሽ መስክረዋል ።  

ARCHIV - Begleitet von Polizisten ziehen Anhänger der rechtsextremen NPD am 07.11.2009 im hessischen Friedberg durch ein Wohngebiet. Der Rechtsextremismus bei Jugendlichen ist nach Einschätzung eines Experten wegen einer neuen Kultur - anders als erwartet - zu einem dauerhaften Problem in Hessen geworden. 797 rechtsextreme Straftaten hatten Hessens Verfassungsschützer bei ihrer Bestandsaufnahme für das vergangene Jahr gezählt. Foto: Boris Roessler dpa/lhe (zu lhe 7250 vom 10.11.2010) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

« አንቱ የተባሉ አዋቂ ና ጎበዝ የህግ ባለሞያ ናቸው ። እንደኔ እምነት ባላቸው የማሳመን ችሎታ ሁላችንም በጋራ በፖለቲካ መድረኮች በምንስማማበት የተሃድሶ ለውጥ ተግባራዊ እንዲሆን ማብቃታቸው የማይቀር ነው ። በመሆኑም እንደኔ እምነት ለዚህ ቦታ የሚመጥኑ ትክክለኛ ሰው ናቸው »

በማሰን የተተኩት ፍሮም ሐምሌ መጀመሪያ ያወጡት ዘገባ የስለላው መስሪያ ቤት ግድያው በድብቅ በሚንቀሳቀሰው ብሄራዊ ሶሻሊስቶች ንቅናቄ በተሰኘው  የአፍቃሪ ናዚዎች ቡድን የበላይነት ሳይፈፀም እንዳልቀረ ነው የሚገልፀው ። ጉዳዩን የተከታተሉት ባለሞያዎች 80 ገፅ ገደማ በሚሆን ሰነድ ያቀረቡት ዘገባ ከ1990 ዎቹ መግቢያ አንስቶ እስካሁን ያለውን የቀኝ አክራሪዎች እንቅስቃሴ የሚዳስስ ነው ። በዚህ ጊዜ በጨቅላ እድሜ ላይ የነበረው የአክራሪነት እንቅስቃሴ በሂደት የኃይል እርምጃን ወደ መውሰድ መሸጋገሩን ሰነዱ ያስረዳል ። ይሁንና ከአንድ አመት በፊት የጀርመን የሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት ይህን ቡድን የአሸባሪዎች መዋቅር ያለው ድርጅት መሆኑን እንደነበረ ለመግለፅ ይፈልግ እንዳልነበረ ነው የሚነገረው ።

የፌደራል ጀርመን የሃገር አስተዳደር ሚኒስትር ሃንስ ፔተር ፍሪድሬሽ ስለ ሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት ሃላፊዎች አሰራር በሰጡት አስተያየት ፤ ባለሥልጣናቱ ቀኝ አይናቸውን መሸፈን ነበር የፈለጉት ይህ ደግሞ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ አይደለም ነው ያሉት ።  ከዚህ በመነሳትም አሰራሩ ተቀባይነት የለውም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል ። ከዚህ ጋር  መስሪያ ቤቱ ስራውን በአግባቡ አልተወጣም ተአማኒነትንም አጥቷል ሲሉ ተናግረዋል ። የሃገር ውስጥ የስለላ ድርጅት የቀኝ አክራሪነትን የተለያዩ ህዋሳት ሳላየው ቀርቼ ነው ቢል ማንም አያምነውም የዶቼቬለው ማርሴል ፍሩስተናው እንደዘገበው ። ለብዙ አመታት ይህን በሚመለከት በሰፊው ዘገባዎች ይቀርቡ ነበር ። ሆኖም ጠበብቱ አደገኛነቱን ከመጠን በላይ አቃለው ነበር የተመለከቱት ። የፊደራሉ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር  እነዚህ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱት ብሄረተኞች ተግባር ሌሎች ወገኖች ሊያደፋፈር ስለሚችል በትጋት ክትትል ማደረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል ። በዓለም አቀፍ ደረጃም የትብብር እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ነው ሃንስ ፔተር ፍሪድሪሽ ያስገነዘቡት

Demonstranten gegen den Neonazi-Aufmarsch halten am Samstag (24.12.2011) in Bielefeld ein Plakat mit der Aufschrift: "Gib Nazis keine Chance" in die Höhe. Etwa 70 Neonazis demonstrierten in Bielefeld gegen das linksgerichtete Jugendzentrum AJZ an der Heeper Straße. Gegen den Aufmarsch der Neonazis hatten sich an verschiedenen Stationen in Bielefeld etwa 6500 Menschen versammelt und demonstrierten überwiegend friedlich. Foto: Oliver Krato / dpa lnw
ምስል picture-alliance/dpa

« ምን ጊዜም የሚቀርበው ጥያቄ የተደራጀ የኃይል እርምጃ መቼ ሊፈፀም ይችላል የሚል ሲሆን ያለምንም ጥርጥር ከብዙ አመታት አንስቶ የሚታወቅና ይህም በአሸባሪነት በኩል ሲከሰት የቆየ ጉዳይ ነው ። NSU ግድያ ከፈፀመ  አንስቶ የታወቀ ነው ። እና እንደሚመስለኝም ይሄ ግድያ የመፈፀሙ ፍላጎት አሁንም ቢሆን አለ ። ስለሆነም ምንጊዜም በትጋት መከታተል አለብን ። ይህን በተመለከተም በአለም ቀቀፍ ደረጃ ተባብረን የቀኝ አክራሪነትንና በተመለከተ አብረን መሥራት አለብን ። በቀኝ አክራሪነት ላይም አለም አቀፍ ትግል እየተካሄደ ነው »

በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ቀኝ አክራሪዎች የሚያደርሱት ጥቃት መጠን ከቀድሞው ብዙም አልተለወጠም ። እጎአ በ 2011 ቀኝ አክራሪዎች 640 የአካል ጉዳት አድርሰዋል ። ይህም ከአቻምናው ጋር ሲነፃፀር በሁለት ይበልጣል ። በ 2011 ፣ 5 የ ግድያ ሙከራዎች ሲመዘገቡ ይህም ከ2010 በአንድ ያነሰ ሆኖ ነው የተገኘው ። በዚሁ አመት 16 ሺህ ሊያስቀጣ የሚችል ጥፋት ማድረሳቸውም ተመዝግቧል ። ከ በዚሁ ዘገባ እንደተመለከተው ከዚህ ውስጥ 70 በመቶው ፕሮፓንግዳ ነው ። የናዚዎች አርማ ያለበት ስንደቅ አላማ በይፋ ማውለብለብ አንዱ መሰል ድርጊት ነው ። የሃገር ውስጥ የስለላ ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ በመላ ጀርመን ያሉት የቀኝ ፅንፈኞች ቁጥር 22,500 ይደርሳል ። ይህም እ.ጎ.አ ከ 2011 በ10 በመቶ የቀነሰ ነው ። ቀኝ አክራሪዎቹ የሚወስዱት እርምጃ ደረጃም በጣም የተለያየ ነው ። ጠበብቱ ትንሽ ቀለል አድርገው የሚያዩትን  ባህርያቸውን ያፈነገጠ ባህል በማለት ይጠቅሱታል ። የዚህ አስተሳሰብ አራማጆች የቀኝ አክራሪዎች  ሙዚቃ የሚያስፋፉ ሲሆን በዚህ ሙዚቃቸው አይሁዶችን የውጭ አገር ተወላጆችን ወይም የግራ ዘመም አቋም ያላቸውን የሚያጥላሉና የሚያንቋሽሹ ናቸው ። ሆኖም ነገ በአዲስ ሃላፊ የሚተኩት የቀድሞው የጀርመን የሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት ሃላፊ ህይንዝ ፍሮም ምስክረነታቸውን እንደሰጡት የቀኝ አክራሪዎች ተከታዮች ቁጥር እየቀነሰ ነው

Berlin/ Bundesinnenminister Hans-Peter Friedrich (CSU), aufgenommen am Montag (02.07.12) im Bundesinnenministerium in Berlin bei einem Statement zum Ruecktritt des Praesidenten des Verfassungsschutzes. Nach der beispiellosen Pannenserie bei den Ermittlungen gegen die Neonazi-Terrorzelle NSU raeumt der Verfassungsschutzpraesident seinen Posten. (zu dapd-Text)
ሃንስ ፔተር ፍሪድሬሽምስል AP

« አብዩ ችግር አክራሪ የኒዮ ናዚ ገፅታ ና አሁንም ቢሆን ያለው አፈንጋጭ ልዩ ባህርይ ያላቸው ክፍሎች ናቸው ። ይህም ከቀኝ አክራሪዎች እምነትና ፍልስፋና ጋር የተገናኘ ነው ። ከብዙ አመታት አንስቶ ስንከታተለው የቆየ ጉዳይ ነው ይሁንና የዚህ አፈንጋጭ ባህርይ ተከታዮች ቁጥር እየተመናመነ በመሄድ ላይ ነው »

።በክፍላተ ሃገር ያሉ መሰል ቡድኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድጋፍ እያጠጡ ነው ። የስለላው ድርጅት እንደመዘገበው ከሆነ አሁን የደጋፊዎች ቁጥር ከ 8300 ወደ 7600 ዝቅ ብሏል ። እነዚህ ቡድኖች ሃሳብ የሚለዋወጡበትን ቅስቀሳ የሚያካሂዱበት ዋናው መሣሪያቸው ኢንተርኔት ነው ። ራሳቸውን ሞት የማይደፍረን የሚሉት አክራሪዎች ይሄን የመገናኛ ዘዴ  በሰፊው ይጠቀሙበታል ከአካባቢም አልፈው ድንበር ዘለል ተሰሚነት ለማግኘት በተጠናከረ መልኩ  አላማቸውን ለማሳካት እየተጠቀሙበት ነው ።

« በኢንተርኔት በመጠቀም የመስፋፋት አላማቸውን እንደሚያሳኩ ያስባሉ ሲመለከቱዋቸው ችቦ የሚያበሩ ና ነጭ ጭምብል ያጠለቁ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የተሰማሩ መስሎ ይታያል ። እንደ ነሱ እምነት የፈዘዘውን ህዝብ ጥፋት የሚያሰጋውን ህዝብ ለመቀስቀስ ና ለማሳየት ነው የሚጥሩት ። ይሁንና ከሚታሰበው በጣም ያነሱ ጥቂቶች ናቸው ። ነገር ግን በቪድዮ በመጠቀም ብዙ እንደሆኑና ትልቅ ንቅናቄ ያለ በማስመሰሉ ረገድ ተሳክቶላቸዋል ። » አላማቸው ህዝብ በብዛት እንዲከተላቸው ለማድረግ ይሁኑ እንጂ በጥቂት መቶዎች የሚቀጠሩ ብቻ እንደሚተባበሩዋቸው ነው ፍርም የሚናገሩት  ።

BERLIN, GERMANY - MAY 01: Sebastian Schmidtke, Chairman of the Berlin branch of the far-right NPD political party, speaks at an NPD rally on the eastern city outskirts on May Day on May 1, 2012 in Berlin, Germany. German lawmakers, following the revelation that two neo-Nazis of the NSU terror group had committed at least nine murders over a multi-year killing spree, are again seeking to ban the NPD. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)
ምስል Getty Images

እነዚህ ቡድኖች ባለፉት ጥቂት ጊዜያት ያለ ፈቃድ በሌሊት ስብሰባ ሲያደረግ ቆይቷል ። ይህን መሰል እንቅስቃሴ ከጀመሩት  መካከል ራሱን የደቡብ ብራብድንቡርግ ተፋላሚ ንቅናቄ ብሎ የሚጠራው ቡድን ይገኝበታል ይህም በቅርቡ በብርንድቡርግ የሃገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር በህግ ታግደል ። በሌላም በኩል 9 የውጭ ተወላጆችና አንድ የጀርመን ፖሊስ በቀኝ አክራሪዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ከታወቀ በኃላ በአንዳንድ ፌደራል ክፍላተ ሃገር መቀመጫዎች ለመያዝ የበቃው ቀኝ አክራሪውን የጀርመን ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እንዲታገገድ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ ውይይቶች ሲካሄዱ ከርመዋል ። በሚቀጥለው አመት በታህሳስ ወር ማብቂያ ላይም 16ቱ የጀርመን ፌደራል ግዛቶች ፓርቲው በህገ መንግሥታዊዊ ፍርድ ቤት እንዲታገድ ለ 2ተኛ ጊዜ ይሞክራሉ ። ፓርቲው ለማሳገድ እጎአ በ 2003 የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል ። ፎርም እንደሚሉት አልሆነለትም እንጂ  ፓርቲው አላማውን ለማሳካት በየጊዜው የህዝብን ስሜት ሊያነሳሱ ይችላሉ ብሎ የሚያምንባቸውን አጀንዳዎች ይዞ ብቅ የሚል ፓርቲ  ነው ።

« NPD እስልምናን በማጥላላት ሁል ጊዜ አንድ ርዕስ ይዞ ለመነሳት ይሞክራል ይeህን ጥላቻ መሰረት በማድረግ ይህን ለመጠቀም ይሞክራል ወደፊትም ቢሆን ይሄ በኤን ፒዴ መነጋገሪያ ሆኖ የሚቀጥል ነው ። ይህን በማስተጋባት በምርጫ የተሳካ ውጤትን ለማግኘት ሊረዳ ይችላል ።  እስካሁን ድረስ አልተሳካላቸውም ግን በመሞከር ላይ ናቸው ። በጣሙን ይሄን ያህል አልተሳካላቸውም ። ስለሆነም በይበልጥ በእለታዊ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ በማትኮር ና ባልተለወጠው ርዕዮታቸውን አቅጣጫ ትግላቸውን እንደቀጠሉ ናቸው ሙከራቸውን እንደቀጠሉ ናቸው ። »

የቀኝ ፅንፈኞችን እንቅስቃሴ መከታተልና በንቃት መጠባበቅ የጀርመን የሃገር ውስጥ የስለላ መስሪያ ቤት ዋነኛ ተግባራት ሆኖ ይቀጥላል ። አዲሱ የመስሪያ ቤቱ ሃላፊም ይህን ሃላፊነታቸውን  በሚገባ ይወጣሉ የሚል ተስፋ ተጥሎባቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ