1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀኝ አክራሪ ሰለባዎች መታሰቢያ

ሐሙስ፣ የካቲት 15 2004

እኢአ ከ2000 እስከ 2007 ዓም በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች በቀኝ አክራሪዎች የተገደሉ የውጭ አገር ዜጎች ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመላው ጀርመን በአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ታስበዋል።

https://p.dw.com/p/148Jw
ምስል dapd

እኢአ ከ2000 እስከ 2007 ዓም በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች በቀኝ አክራሪዎች የተገደሉ የውጭ አገር ዜጎች ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመላው ጀርመን በአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ታስበዋል። በመስሪያ ቤቶች፣ በድርጅቶች እና ተቋማት ይህችን ደቂቃ ሟቾቹን በማሰብ እንዲያሳልፉ በተጠየቁት መሰረት አካኪደዋል። ባቡሮች እና አውቶቢሶች ለአንድ ደቂቃ ከእንቅስቃሴ ተገትተዋል። የመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ የመክፈቻ ንግግር አስቀድሞ የተያዘው ባለፈው ሳምንት ስልጣን ለቀቁት ቀድሞው የጀርመን ፕሬዚዳንት ክርስትያን ቩልፍ ነበር። ሆኖም ከስልጣን በመውረዳቸው መራይተ መንግስቷ አንጌላ መርክል ነበሩ ንግግሩን ያደረጉት።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ