1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተፈረደባቸዉ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 6 2010

በ1970 የጎጃም ክፍለ ሐገር የደርግ አባል የነበሩት መቶ አለቃ እሸቱ ሰባ-አምስት ሰዎችን ገድለዋል፤ ከሁለት መቶ ሃያ የሚበልጡትን ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዉጪ አስረዋል፤ አሰቃይተዋልም የሚል ክስ ተመስርቶባቸዉ ሲከራከሩ ነበር።

https://p.dw.com/p/2pSB0
Äthiopien Opfern der Derg-Herrschaft
ምስል DW/J. Jeffrey

MMT (Q&A) Eshetu Alemu-Urteil - MP3-Stereo

ኔዘርላንድስ የሚኖሩት የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት (የደርግ) ከፍተኛ ባለሥልጣን  መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ በዘመነ ሥልጣናቸዉ ለፈፀሙት በደል ዕድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸዉ። በ1970 የጎጃም ክፍለ ሐገር የደርግ አባል የነበሩት መቶ አለቃ እሸቱ ሰባ-አምስት ሰዎችን ገድለዋል፤ ከሁለት መቶ ሃያ የሚበልጡትን ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዉጪ አስረዋል፤ አሰቃይተዋልም የሚል ክስ ተመስርቶባቸዉ ሲከራከሩ ነበር። ዛሬ ዘ-ሔግ ኔዘርላድስ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በተያዘባቸዉ የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ጥፋተኝነታቸዉን አረጋግጦ እድሜ ልክ ዕስራት ፈርዶባቸዋል። የፍርዱን ሒደት የተከታተለዉን ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋንና አንድ የዓይን ምሥክርን በሥልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ