1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ የጀርመን ፕሬዝደንት ሮማን ሔርሶግ ዜና ረፍት

ሐሙስ፣ ጥር 4 2009

የቀድሞዉ የጀርመን ፕሬዝደንት ሮማን ሔርሶግ ሞቱ።82 ሁለት ዓመታቸዉ ነበር።ሔርሶግ ጀርመን ዳግም ከተዋሐደች በኋላ እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር ከ1994 እስከ 1999 የጀርመን ፕሬዝደንት ነበሩ።

https://p.dw.com/p/2VadS
Deutschland Altbundespräsident Roman Herzog ist tot
ምስል Getty Images/A. Rentz

የቀድሞዉ የጀርመን ፕሬዝደንት ሮማን ሔርሶግ ሞቱ።82 ሁለት ዓመታቸዉ ነበር።ሔርሶግ ጀርመን ዳግም ከተዋሐደች በኋላ እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር ከ1994 እስከ 1999 የጀርመን ፕሬዝደንት ነበሩ።አሁን ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል የሚመሩት የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት (CDU) አባል የነበሩት ሔርሶግ ፕሬዝደንት ከመሆናቸዉ በፊት የጀርመን ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ በመሆን አገልግለዋል።በዘመነ ሥልጣናቸዉ የምጣኔ ሐብት እና የፖለቲካ ተሐድሶ እንዲደረግ ከፍተኛ ግፊት ያደርጉ የነበሩ ፖለቲከኛ ነበሩ።መራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ሔርሶግን ሐገራቸዉን በተለያዩ ደረጃዎች ያገለገሉ፤«አርበኛ፤ግልፅ፤ቀልደኛ እና ተግባቢ» በማለት አድንቀዋቸዋል።ፕሬዝደንት ዮአኺም ጋዉክ በበኩላቸዉ የጀርመን እና የሕዝቧን ሥም ለማደስ ከፍተኛ አስተዋፅ ያደረጉ፤ ማራኪ ስብዕና የተላበሱ ብለዋቸዋል።

ነጋሽ መሃመድ

አዜብ ታደሰ