1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሽኝት ሥነ-ስርዓት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 17 2010

በኢትዮጵያ ሀገርን በመምራት ስልጣን ላይ ቆይተው በክብር ለመሸኘት ዕድል ያገኙት አሁን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለመባል የበቁት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎች ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/2weDR
Äthiopien Addis Abeba Abschied ehemaliger Ministerpräsident Haile Mariam Desalegn
ምስል DW/G. Tedla

«አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣንና ወንበር ህዝብ ማገልገያ እንጂ የግል መገልገያ መሆን እንደሌለበት ያስተማሩ ናቸው።»

በትናንትናው ዕለት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ለቀድሞው የስልጣን አቻቸው አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ለባልተቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የክብር የሽኝት ስነ ስርዓት አድርገዋል። ሽልማትም ሰጥተዋል። እንዲያም ሆኖ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሽልማት መሰጠቱ የተለያየ አመለካከት አስከትሏል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ