1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀጠለው የኮንሶ እና አሌ ግጭት

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ ዳግም ባገረሸ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። የአካባቢው ነዋሪዎች አንዳሉት ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ዛሬ ድረስ ሰዎች እየሞቱ መንደሮችም እየተቃጠሉ ይገኛሉ ።

https://p.dw.com/p/3iVPe
Äthiopien Konflikt zwischen Konso & Ale
ምስል Ale Communication Office

የቀጠለው የኮንሶ እና አሌ ግጭት

በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ ዳግም ባገረሸ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። የአካባቢው ነዋሪዎች አንዳሉት ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ዛሬ ድረስ ሰዎች እየሞቱ መንደሮችም እየተቃጠሉ ይገኛሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት በበኩላቸው በአካባቢው የተከሰተው ግጭቱ እየሰፋ ፣ ችግሩን ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ በአካባቢው ዳግም ላገረሸው ግጭት አንዳንድ ያላቸውን የቀበሌ አስተዳዳሪዎችንና የፖለቲካ አመራሮችን ተጠያቂ አድርጓል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 
አዜብ ታደሰ