1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቃዛፊ ሙት ዓመትና የድሕረ-ቃዛፊዋ ሊቢያ

ሰኞ፣ ጥቅምት 12 2005

ሁሉምበየተቃዋሚዎቻቸዉ ሲሸነፉ ግን ሥልጣን ሐገራቸዉን አንድም ለየአሸናፊዎቻዉ እየጣሉ ተሰደዱ፣ ሁለትም እየተማረኩ ታሰሩ፣ ሰወስትም የፍርዱ ሒደት ምንም ይሁን ምን እየተፈረደባቸዉ ተገደሉ እንጂ ጦር ሜዳ፥ ቆስለዉ፥ ተማርከዉ ያልፍርድ አልተገደሉም።

https://p.dw.com/p/16UiP
A woman celebrates on the streets after casting her vote during the National Assembly election in Tripoli's Martyrs square July 7, 2012. Crowds of joyful Libyans, some with tears in their eyes, parted with the legacy of Muammar Gaddafi on Saturday as they voted in the first free national election in 60 years. REUTERS/Zohra Bensemra (LIBYA - Tags: ELECTIONS POLITICS)
አዲሲቱ ሊቢያ ምርጫምስል Reuters


22 10 12


የበሽር አል-አሰድ ፍፃሜ እንደ ቤን ዓሊ ስደት፣ እንደ ሙባረክ ወሕኒ ቤት፣ እንደ ሳዳም ስቅላት፣ ወይም እንደ ጋዳፊ ርሸና መሆን አለመሆኑ በርግጥ አለየም።የዉጪ ጠላቶታቸዉም፤ የሐገር ዉስጥ ተፋላሚዎቻቸዉ በተደጋጋሚ እንደዛቱት ግን አሰድ ከቀዳሚዎቻቸዉ እንዳዱ የሚፈፀሙበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።ጠላት ተፋላሚዎቻቸዉ ፍላጎት፣ ዕቅድ፣ ዛቻቸዉን ገቢር ለማድረግ ሲረባረቡ፣ የዛሬዉ ተረኛ አሰድ፣ በአምናዉ ባለተራ በቃዛፊ ግድያ በስሱም ቢሆን እጃቸዉ እንዳለበት ተዘገበ።ዘገባዉ ዓለም፣ ዓረብን ጉድ አጃኢብ እንዳሰኘ ቃዛፊ የተገደሉበት አንደኛ ዓመት ደፈነ።የቃዛፊ ሙት አመት መነሻ፣ የግድያዉ ሴራ ማጣቀሻ፣ የድሕረ ቃዛፊዋ ሊቢያ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።


የሃያ አመቱ የሕክምና ተማሪ አሕመድ ዛዋቢ የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን ታማኝ ጦር ለመዋጋት እንደ ብዙ የእድሜ አቻዎቹ እስኪሪብቶ ደብተሩን አስቀምጦ መትረየስ-ጠመንጃ፥ ጥይት ቦምብ ከታጥቀ አምና ጥቅምት ስድስተኛ ወሩን አስቆጠረ።

የሚስራታ ተወላጅ የሚስራታ አካባቢ ሚሊሺያ አባል ነበር።«ቃዛፊ መማረካቸዉን ጓደኞቻችን በስልክ ሲነግሩን» ሁላችንም ወደ አካባቢዉ እየሮጥን ሄድን» አለ ወጣቱ በቀደም ዘ-ጋርዲያን ለተሰኘዉ ጋዜጣ ዘጋቢ።ብዙ ሰዎች ተሰብስበዉ ይንጫንጫጫሉ።ቃዛፊ አዉራ መንገዱ መሐል ነበሩ።ጠጋ ስል የተመዘዘ ሽጉጥ አየሁኝ።ሽጉጡን የያዘዉን እጅ አየሁት።ወዲያዉ ተኩስ ሰማሁኝ።

የሲርቱ ቆፍጣና ወታደር፣ የአርባ ሁለት ዓመቱ የሊቢያ አብዮታዊ ገዢ፣ የአፍሪቃ ንጉሠ-ነገስት ታላቁ ወድም ቃዛፊ ከአልባሌ ቱቦ አጠገብ፣ በጠራራ ፀሐይ አዉራ መንገድ ላይ ተደፉ።ጥቅምት አስር ሁለት ሺሕ አራት።

ከኢዲ አሚን ዳዳ እስከ ሚልተን ኦቦቴ፣ ከሂስኒ ሐብሬ እስከ ጉኩኒ ወዴ፣ ከዚያድ ባሬ እስከ መንግሥቱ ሐይለ ማርያም፣ ከሞቡቱ ሴሴ ሴኮ እስከ....እስከ ኒኮላ ቻዉቼስኮ፥ ከኤሪኽ ሆኔከር እስከ ስሎቮዳን ሜሎሶች፥ ከሳዳም ሁሴይን እስከ ከቻርልስ ቴለር፣ እስከ ሎራ ባግቦ የነበሩ መሪዎች ከየጠላት ተቃዋሚዎቻቸዉ ጋር ተዋግተዉ ወይም ተሟግተዉ ተሸንፈዋል።ቤን ዓሊና ሙባረክ በሕዝብ አመፅ ተወግደዋል።

ሁሉም አምባገነኖች፥ ሕዝባቸዉን ረግጠዉ የገዙ፥ ተቃዋሚ-ተቺዎቻቸዉን ያለምሕረት የሚገድሉ እንደነበሩ ብዙ አያጠያይቅም።በየተቃዋሚዎቻቸዉ ሲሸነፉ ግን ሥልጣን ሐገራቸዉን አንድም ለየአሸናፊዎቻዉ እየጣሉ ተሰደዱ፣ ሁለትም እየተማረኩ ታሰሩ፣ ሰወስትም የፍርዱ ሒደት ምንም ይሁን ምን እየተፈረደባቸዉ ተገደሉ እንጂ ጦር ሜዳ፥ ቆስለዉ፥ ተማርከዉ ያልፍርድ አልተገደሉም።

የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ የአርባ ሁለት ዓመታት ያገዛዝ ሥልት ምግባርም ከሌሎቹ አምባገነኖች የተለየ ብዙም የተለየ አልነበረም።የዘመነ-ሥልጣናቸዉ ፍፃሜ ግን ልዩ ነዉ።አሟሟታቸዉ ደግሞ የዓለም ሕግ፣ ደንብ ወይም ስምምነትን ገቢራዊነት አጠያያቂ አድርጎታል።

«ገዳዩን በትክክል አይቼዋለሁ።» አለ የያኔዉ የሚስራታ ተዋጊ ዘዋዲ «የመጀመሪያ ስሙንም አዉቀዋለሁ።» ቀጠለ ወጣቱ በቀደም።«ገዳዩ ማ ነዉ?» «መናገር አልችልም።» መለሰ።ያኔ ግን ማንም ሳይጠይቀዉ ገዳይ እኔነኝ እያለ የፎከረ፣ ከጋዛፊ በማረኩት ሽጉጥ ጋዛፊን ገደልኩ እያለ፣ቆስሎ የተማረከ የስልሳ ዘጠኝ ዓመት አዛዉንት የመግደል ድል-ጀግንነቱን ካሜራ ፊት የዘረዘረ ግለሰብ ነበር።

ኦምራን ሻዕባን የቃዛፊ ገዳይ ነኝ ካሉት ወይም ገዳይ ናቸዉ ተብለዉ ከሚጠረጠሩት የሚሊሻ አባላት አንዱ ነበር።የአስራ-ስምንት አመት ወጣት፥ የሚስራታ ሚሊሺያ አባል።ኦምራን ባለፈዉ ሐምሌ በኒ ዋሊድ በተባለዉ አካባቢ የሚኖሩ የሙዓመር ቃዛፊ ደጋፊ የጎሳ ታጣቂዎች አግተዋቸዋል የተባሉ የሚስራታ አካባቢ ነዋሪዎችን እንዲያስለቅቅ የተላከዉ የሚስራታ የሚሊሻ ቡድን አባል ሆኖ ወደ በኒ ዋሊድ ተላከ።

ያ ወጣት አምና ጥቅምት የቃዛፊ ገዳይ ነኝ እያለ ሲፎክር አይተዉት የነበሩ የበኒ ዋሊድ ታጣቂዎች አገቱት።አጋቾች ወጣቱን ለሐምሳ ሰባት ቀናት ሲደድቡ፥ ሲያሰቃዩት ቆይተዉ ከብዙ ድርድር በሕዋላ ለቀቁት።ቀጣቱ ክፉኛ በመቁሰሉ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ፓሪስ ተላከ።አልዳነም።

የግብፅ፥ የብሪታንያ፥ የኢጣሊያና የፈረንሳይን መገናኛ ዘዴዎች ትኩረትን የሳባዉ ግን የቃዛፊ ገዳይነኝ ባዩ ወጣት ሞት ሳይሆን የቃዛፊ አሟሟት ነበር።የግብፅ ቴሌቪዥን ጣቢያ፥ ዴይሊ ቴሌግራፍ የተሰኘዉ የብሪታንያ ጋዜጣና ኮሪየሬ ደላ ሴራ የተባለዉ የኢጣሊያ ጋዜጣ በየፊናቸዉ እንደዘገቡት ቃዛፊን ከቆሰሉ፥ ከተማረኩ በሕዋላ በጠረራ ጸሐይ ያስገዳለቸዉ ከሊቢያ ሕዝብ የቀመቱን ገንዘብ የቀድሞዉ የፈረንሳይ የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ኒኮላ ሳርኮዚ ለፕሬዝዳትነት እንዲመረጡ መስጠታቸዉ ወይም ሰጥቻለሁ ማለታቸዉ ነዉ።

ቃዛፊ ልጃቸዉ ቤት እያሉ የኔቶ አዉሮፕላኖች የጣለባቸዉ ቦምብ ልጅ፥ የልጅ ልጆቻቸዉን ገደለ እንጂ እሳቸዉን አልነካም።ትሪፖሊ ቤተ-መንግሥታቸዉን በከፊል ካወደመዉ ቦምብም ተርፈዋል። ሰዉዬዉ ተማርከዉም፥ ሆነ ተሸሽገዉ በሕይወት ከቆዩ የተናገሩትን የሚያረጋግጥ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ።ይሕ ለፕሬዝዳት ሳርኮዚ አደገኛ ነበር።

ሳርኮዚ ዘገቦቹ እንደጠቆሙት አንድ አማራጭ ግን ነበራቸዉ።የቃዛፊን አድራሻ ማግኘት።የሊቢያ የሽግግር መንግሥት የስለላ ጉዳይ የበላይ የነበሩት ራሚ ኤል ኦቤይዲ እንደሚሉት ለቃዛፊ መገደል የፈረንሳይ የስለላ ድርጅት ከፍተኛዉን ሚና ተጫዉቷል።የሽግግር መንግሥቱ ጠቅላይ ሚንስትር ማሕሙድ ጅብሪሊም ከስለላ ሚንስትራቸዉ አባባል ጋር ይስማማሉ።

ነገሩ እንዲሕ ተፈፀመ።

ቃዛፊ ከትሪፖሊ ከተባረሩ በሕዋላ መግለጫ የሚሰጡት ከሶሪያ ለሚያሰራጭ ራይ ለተሰኘዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነበር።በስልክ።የሶሪያዉ ፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድ ደግሞ የቃዛፊ ዕጣ እንዳይገጥማቸዉ የሚፍጨረጨሩበት ወቅት ነዉ።ሳርኮዚ «የቃዛፊን የሳተላይት ስልክ ቁጥር ከሰጡን ፈረንሳይ በርሶ መንግሥት ላይ ፖለቲካዊ ጫና አታደርግም» አሏቸዉ አሉ።አሰድ አላመነቱም።

የሳተላይት ስልክ ቁጥሩ ሊቢያ ለሚገኙት የፈረንሳይ ሰላዮች ተላከ።ጥቅምት አስር በሊቢያ አቆጣጠር ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት።የቃዛፊ የሳተላይት ቁጥር ሲደወል ሰዉዬዉ ያሉበት አካባቢ ታወቀ።ሲርት አጠገብ ናቸዉ።ከጥቂት ሰዓታት በሕዋላ ቃዛፊን ያጀበዉ ቅፈለት በኔቶ ሚሳዬልና የአዉሮጳላን ቦምብ ተደበደበ።የሚስራታ ሚሊሻዎች ወደ አካባቢዉ እንዲሔዱ ታዘዙ።

ስድስት ሰዓት ግድም ሚሊሻዉ አካባቢዉን ሲከብ ቱቦ ዉስጥ የተወሸቁት ሰዎች አንድ በአንድ እጃቸዉን ሽቅብ እየሰቀሉ ተማረኩ።ከተማራኪዎቹ መሐል ፊቱ በደም የተጨማለቀዉ እሳቸዉ ነበሩ።ቃዛፊ።ወዲያዉ ተገደሉ።ባለፈዉ ቅዳሜ አመቱ።

ሳርኮዚ በርግጥ ሥልጣን ላይ የሉም።የአሰድ የሥልጣን ገመድ አልተበጠሰችም ግን መንምናለች።ሶሪያ በዉጊያ ትወድማለች።የበሽር አል-አሰድን ሥርዓት በሐይል ለማስወገድ ለሚፋለሙት ሐይላት ጠቀም ያለ ገንዘብ ከሚያፈሱት የአረብ መንግሥታት አንዱ የትሪፖሊ መንግሥት ነዉ።

የመሐመድ አል ማጋሪያፍ መንግሥት ለሶሪያ አማፂያንን ገንዘብ ሲሰጥ፥ ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን ለማስወገድ የተዋጉ አማፂያን በተለይም ሙስሊም ፅንፈኛ የሚባሉት ሐይላት ደግሞ ሶሪያ ድረስ ዘምተዉ፥ ቃዛፊን ለማስገደል የተባበሯቸዉን አል-አሰድን ለማስወገድ በነፍጥ ይፋለማሉ።

ሊቢያ ራሷ ደግሞ በጎሳ ታጣቂዎች ግጭት፥ በፖለቲከኞች ሽኩቻ ግራ ቀኝ ትላጋለች።ባለፈዉ ሐምሌ መጀመሪያ ሊቢያ ዉስጥ የተደረገዉ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ምርጫ አርባ ሁለት ዘመን በአንድ አምባ ገነን ሥትገዛ የነበረችዉን’ ሐገር ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የመጀመሪያዉ ጥሩ እርምጃ ነበር።

ከምርጫዉ በሕዋላ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን የያዙት ሙስጠፋ አቡ ሻጉር ለሚንስትርነት ያቀረቧቸዉን ፖለቲከኞች ሹመት ምክር ቤቱ ሁለቴ ዉድቅ ሥለደረገባቸዉ ባለፈዉ መስከረም አስራ-ሰባት ከጠቅላይ ሚንስትርነቱ ሥልጣን ተባረዋል።ሻጉር ሥልጣን በያዙ በሁለተኛ ወሩ ከስልጣን መባረራቸዉ የሰሜን አፍሪቃ የፖለቲካ ጉዳይ አጥኚ ኢማድ ኤል አኒስ እንደሚሉት የዲሞክራሲ አንዱ ገፅታ ነዉ።

ቃዛፊን ከሥልጣን ለማስወገድና ለማስገደል በግንባር ቀደምትነት የተዋጉት የሚስርታ ወይም የቤንጋዚ አካባቢ ጎሳ ታጣቂዎችና ፖለቲከኞች ገሚሱ የሊቢያን የሽግግር መንግሥትን ከሪፖሊ ሲመሩ፥ገሚሱ ቤንጋዚ ላይ የራስ ገዝ መስተዳድር አዉጀዉ ነበር።

የግዛቲቱ ሕዝብ የራሱን ነፃ መንግሥት መመሥረት መፈለግ አለመፈለጉን በሕዝበ-ዉሳኔ ለማስወሰን እንደሚፈልጉም በተደጋጋሚ አስታዉቀዋል።የቃዛፊ ደጋፊ የሚባሉት የሲርትና የበኒ-ዋሊድ አካባቢ የጎሳ አባላትና ፖለቲከኞች በፊት በሽግግር መንግሥቱ፥ ካለፈዉ ሐምሌ ወዲሕ ደግሞ በጊዚያዊ መንግሥቱ ዉስጥ ሥልጣን እንዳይኖራቸዉ አበክረዉ የሚታገሉትም እኒያዉ ከሊቢያ ማዕከላዊ መንግሥት ለመገንጠል የሚፈልጉት የቤንጋዚና የሚስራታ አካባቢ ፖለቲከኞች መሆናቸዉ ነዉ እንቆቅልሹ።

በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጡ ምሥራቅና ምዕራብ ተብሎ በሚከፈለዉ በቤንጋዚ-ሚስራታ እና በሲርት-በኒ ዋሊድ አካባቢ የሚኖሩት ፖለቲከኞች ዉዝግብ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ አቡ ሻጉር አዲሱ ወንበራቸዉን ተደላድለዉ ሳይቀመጡበት አስፈንጥሮ ጥሏቸዋል።

የአቡ ሻጉር መባረር ለፖለቲካ አዋቂ ኤል-አኒስ የዲሞክራሲ ምልክት የመሆኑን ያክል ለሌላኛዉ የፖለቲካ ተንታኝ ለዓሊ አልጊብሺ ደግሞ የጎሳ ልዩነት ደም ያቃባቸዉ ፖለቲከኞች ሽኩቻ ዉጤት ነዉ።


«አሁን ያለዉን ልዩነት ለማጥበብ በተለያዩ ፖለቲካዊ ሐይላት መካካል መግባባት መኖር አለበት።ይሕ ግን አይታይም።በተለያዩ ወገኖች ወይም ፓርቲዎች መካካል የሚደረገዉ ፖለቲካዊ ፍልሚያ በጣም ሐይለኛ ነዉ።ይሕ መቃለል አለበት።እንደዚሕ አይነት ፈተናዎችን ሊያስወግድ የሚችል መንግሥት ሊኖር ይገባል።ሥለ ሊቢያ ማሰብ ያስፈልጋል።ሐገሪቱ አሁን የምትሻዉ እንዲሕ ዓይነት ሥለ መላዋ ሊቢያ የሚያስብ ነዉ።»

አቡ-ሻጉርን ከስልጣን ያበረረዉ አዲሱ ምክር ቤት ትናንት በተቃዋሚ ሰልፈኞች ተወርሮ ነበር።ከፈጣሪ ሌላ፥ ሌላ ፈጠሪ የለም፥ ፕሬዝዳት መሐመድ ማጋሪፍ የፈጣሪ ጠላት ነዉ የሚል መፈክር እያስተጋባ ወደ ምክር ቤቱ አዳራሽ የተመመዉ ከአምስቶ እንደሚበልጥ ተገምቷል።

የሕዝቡ ተቃዉሞ የሚስራታ-ቤንጋዚ ሚሊሻዎች የበኒ ዋሊድ ሕዝብን መግደል ማሰቃየታቸዉ የፕሬዝዳት ማጋሪፍ መንግሥት አላስቆመም የሚል ነዉ።በሊቢያ መከላከያ ሚንስትር ይደገፋሉ የሚባሉት የቤንጋዚ-ሚስራታ ሚሊሻዎች የቃዛፊ ደጋፊዎች የሚሏቸዉን በኒ ዋሊድንና አካባቢዉን በተከታታይ በከባድ መሳሪያ ይደበድባሉ።

እስካለፈዉ ቅዳሜ ድረስ በድብደባዉ ሃያ-ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።ከተገደሉት አንዱ የኮሎኔል ሙዓመር የመጨረሻ ወንድ ልጅ ነዉ ተብሏል።ከሁለት መቶ በላይ ቆስለዋል።የትሪፖሊ ነዋሪዎች የሐገሪቱን ፓርላሚ ሲወሩ የትናንቱ የመጀመሪያዉ አይደለም።ባለፈዉ መስከረም ሃያ አራትም አካባቢያችን በምክር ቤቱ ዉክልና አላገኘም ያሉ ተቃዋሚ ሠልፈኞች ምክር ቤቱ ወርረዉ የምክር ቤቱን አባላት አዉግዘዉ ነበር።

ቤንጋዚ ዉስጥም የተቃዉሞ ሠልፍ ነበር።የተቃዉሞዉ ሰበብ አል-አሕራር የተባለዉ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚስራታ-ቤንጋዚ ታጣቂዎች በኒ ወሊድ ላይ ባደረሱት ድብደባ የቃዛፊን ልጅ ጨምሮ በርካታ ሰዉ መገደል፥ መቁሰሉን መዘገብ የለበትም የሚል ነዉ።አራት መቶ የሚሆኑ ተቃዋሚዎች የቴሌቪዥን ጣቢያዉን ሕንፃ ወረዉ ጣቢያዉን ከነባለቤቱ አዉግዘዋል።

የቃዛፊ መገደል የፓሪስ-ዋሽግተን፥ የንደን-ቤንጋዚ ፖለቲከኞች ያኔ እየተቀባበሉ እንዳሉት ለሊቢያ ዳግም ነፃ ከመዉጣት እኩል የሚቆጠር ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርና ሌሎች ሰወስት ዜጎችዋ የተገደሉት ዳግም ነፃ በወጣችዉ ሊቢያ ዉስጥ ነዉ።ያዉም የዳግማዊ ነፃነትዋ የነፍጥ ዉጊያ በተጀመረበት፥ ለምዕራባዉያን የቦምብ ሚሳዬል ድብደባ ሰበብ በሆነችዉ ቤንጋዚ ዉስጥ።


ሊቢያዉያንም ዳግም ነፃ በወጣችዉ ሐገራቸዉ የታጠቁት እርስ በርስ ይጋደላሉ፥ አንዱ የሌላዉን ወገን ያግታል፥ ብዙ ሰዉ ያለፍርድ ይታሰራል፥ ይገደላል፥ ይሰወራልም።ዓሊ አል-ጊብሺ ፈጣን መፍትሔ የሚያሻዉ ችግር ይሉታል።

«የፀጥታዉ ሁኔታ ባጠቃላይ ሲታይ ሊቢያ ነፃ ከወጣች ወዲሕ በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት በጣም ተበለሻሽቷል።በተለያዩ የሊቢያ ግዛቶች የሚገኙ የተለያዩ ታጣቂዎች ይጋጫሉ።ሰዎች ይታገታሉ።ይታሰራሉ።ይሰወራሉም።ይሕ ፀጥታን፥ ሕግና ሥርዓትን የማስከበሩ ጉዳይ ፈጣን እርምጃ የሚያስፈልገዉ ነዉ።»

የሊቢያ ትርምስ ዳፋዉ ለብዙዎቹ የአፍሪቃ ሐገራት በጣሙን ለሰሜን ምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት መትረፉ ነዉ-የአፍሪቃዉያን ጭንቅ።ሐብታሚቱ አረብ-አፍሪቃዊቱ ሊቢያ በምዕራባዉያን ጦር ሐይል ድብደባ ዳግም ነፃ ከመዉጣትዋ በፊት የአፍሪቃ ሕብረትን አመታዊ በጀት አስራ-አምስት በመቶ ትሸፍን ነበር።ዛሬ-ዜሮ።

የቃዛፊዋ ሊቢያ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን የሚሰሩ፥ የሚኖሩባት ነበረች።ዛሬ ገሚሱ የጥይት፥ ሌላዉ የባሕር፥ የተቀረዉ የበረሐ ሲሳይ ሆኗል።እድለኛዉ ዳግም ተሰዷል ወይም ወደ ችግረኛ ሐገሩ ተመልሷል።የቃዛፊዋ ሊቢያ በብዙ የአፍሪቃ ሐገራት ሥራ ላይ ታዉለዉ የነበረዉ ገንዘብ እንደተቋረጠ ነዉ።

መንበሩን ኑዮርክ ያደረገዉ ዳሚና የተሰኘዉ የአፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ጉዳይ ተንታኝ ተቋም ባልደረባ ሳባስቲያን ስፒዮ-ግራብራሕ እንደሚሉት ሊቢያ ከስራለች።

«ሐገሪቱ አሁን ገንዘብ የላትም።የነዳጅ ኢንዱስትሪዋ እንደፈራረሰ ነዉ የሚሰለዉ።ፀጥታዉ በጣም መጥፎ ነዉ።እና ከሊቢያ ወደተቀሩት የአፍሪቃ ሐገራት የሚፈስ መዋዕለ ንዋይ ምንም የለም ማለት ይቻላል።»

ችግሩ የጠናዉ ማሊ ላይ ነዉ።የቃዛፊዋ ሊቢያ ያስጣጋች፥ የረዳች፥ ያስታጠቀቻቸዉ የቱአሬግ ተወላጆች ከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ ማሊ ገብተዉ ለነፃነት እየተፋለሙ ነዉ።ቃዛፊ ያጠራቀሙትን የጦር መሳሪያ ዘርፈዉ ወይም ከዘራፊዎች በርካሽ ገዝተዉ የታጠቁት የማሊ አክራሪ ሙስሊሞች፥ ከቱአሬግ አማፂያን ጋር አብረዉ ሰሜናዊ ማሊን ይቆጣጠራሉ።አማፂያኑን ለማስወገድ፥ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ጦር ማዝመት፥ የአፍሪቃ ሕብረት ፖለቲካዊ ድጋፍ መስጠት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገንዘብ ማዉጣት አለበት።ከዚያስ፥ ሲሆን ለመስማት ያብቃን።

TO GO WITH STORY BY INES BEL AIBA This picture shows a view of the town of Bani Walid on January 26, 2012. Residents of the Libyan oasis town, a long standing bastion of Kadhafi's regime, are resigned to the country's new leadership but say the slain dictator lives on in their hearts. AFP PHOTO/MAHMUD TURKIA (Photo credit should read MAHMUD TURKIA/AFP/Getty Images)
ባኒ ዋሊድምስል Getty Images
epa02975684 A Libyan rebel fighter paints on the wall of one of the pipes where Muammar Gaddafi allegedly found hiding, in Sirte, Libya, 21 October 2011. Libyan deposed leader Muammar Gaddafi was arrested on 20 October, some witnesses said he was found hiding in a drainage pipe in Sirte. He died later, along with his son Motassim. EPA/GUILLEM VALLE +++(c) dpa - Bildfunk+++
የቃዛፊ የመጨረሻ ምሽግምስል picture alliance/dpa
In this image taken from video on Sunday, June 12, 2011, provided by FIDE President Kirsan Ilyumzhinov's press service, Libyan leader Moammar Gadhafi, next to visiting president of the World Chess Federation Kirsan Ilyumzhinov, not in photo, before a game of chess in Tripoli, the capital of Libya. As the world awaits Moammar Gadhafi's next move, the Libyan leader has been playing chess with the visiting Russian head of the World Chess Federation. The federation is headed by the eccentric Kirsan Ilyumzhinov, who until last year was the leader of Russia's predominantly Buddhist republic of Kalmykia. He once claimed to have visited an alien spaceship. (Foto:FIDE Press service/AP/dapd) EDITORIAL USE ONLY
ቃዛፊ እንደ መሪምስል AP

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ
































ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ