1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቆዳ እና ቆዳ ውጦቶች ኤግዚቢሺን በአዲስ አበባ

ረቡዕ፣ የካቲት 12 2006

ኢትዮጵያ እጅግ ደሀ ከሚባሉት ጥቂት የዓለማችን ኣገሮች መካከል ብትመደብም በሌላ ጎኗ ደግሞ በተፈጥሮ ኃብት የበለጸጉ ከሚባሉት አካባቢዎች መካከልም ያንኑ ያህል ትጠቀሳለች። ለዓብነት ያህልም ለግብርና ምቹ በሆነ ሰፊ መሬት የታደለችው ኢትዮጵያ በቡና ምርትም ቀዳሚ ከሚባሉት መካከል ስትሆን በእንስሳት ሀብቷም እንዲሁ ከዓለም 10ኛ ናት።

https://p.dw.com/p/1BBYW
Markt in Dhaka Bangladesch
ምስል Munir Uz Zaman/AFP/Getty Images

ከኣፍሪካ ደግሞ 1ኛ። ከዚሁ የተነሳ በከፍተኛ መጠን ወደ ውጪ ከምትልካቸው ምርቶች መካከልም ቆዳና ሌጦ ኣንዱ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ከጥሬ ቆዳ ይልቅ በከፊል የተቀየሩ ወይንም ወደ ቆዳ ውጤቶች የተለወጡ ሸቀጦችን ወደመላክ እያዘነበለች መምጣቷ ይነገርላታል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ኣንድ ዓለም ዓቀፍ የቆዳ ውጤቶች ኤግዚቢሺን በአዲስ አበባ ይካሄዳል። እኛም ይህንኑ ከነገ ጀምሮ እስከ ፊታችን ቅዳሜ ድረስ ለሶስት ቀናት በሚሊኒየም ኣዳራሽ የሚካሄደውን የቆዳ ውጦቶች ኤግዚቢሺን ኣስመልክተን ለዛሬው የኢኮኖሚ ዝግጅታችን ያዘጋጀነውን እንሆ ይዘን ቀርበናል፤ ጤና ይስጥልኝ የተወደዳችሁ የዶቸቬሌ ታዳሚዎች ከዝግጅቱ ጋር ጃፈር ዓሊ ነኝ መልካም ቆይታ።

Symbolbild Handtasche
ምስል Fotolia/Africa Studio

ለመሆኑ የዚህ የቆዳ ውጤቶች ኤግዚቢሺን ዓላማ ምንድነው? አቶ አብዲሳ አዱኛ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ዋ/ጸሓፊ

አቶ አበበ ተክሉ ደግሞ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ሊቀመንበር እና በግሉ ዘርፍም የጥቁር ዓባይ ቆዳ ፋብሪካ ዋ/ስራ ኣስኪያጅ ናቸው።

Flash-Galerie Oktoberfest 2009
ምስል AP

አቶ ኢስጢፋኖስ ሳሚኤል በዚህ በጀርመን ኣገር የኢትዮጵያ እና የጀርመን የኢኮኖሚ ኮንፍረንሶች ዝግጅት ዋና ኃላፍ ናቸው። ዓላማቸውም የኢትዮጵያን እና የጀርመንን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ግንኙነት ማዳበር ሲሆን ነገ በአዲስ አበባ በሚከፈተው እና ኢሊያ ተብሎ በሚታወቀው የቆዳ ውጤቶች ኤግዚቢሺን ላይም የጀርመን ኩባኒያዎች እንሳተፉ መጋበዝ ነው።

ኢትዮጵያ፤ በግብርና ሚ/ር ዓኃዛዊ መረጃዎች መሰረት፤ 60 ሚሊየን ያህል ከብቶች እና 50 ሚሊየን ገደማ በግና የሎች እንዲሁም ከ2,3 ሚሊየን በላይ ግመሎች እንዳሏት ይገመታል። ከዚሁ የተነሳ ኣገሪቱ ቀዳሚ ትኩረት ከምትሰጣቸው ስምንት የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል ኣንዱ ይኸው የቆዳ ዘርፍ ነው። በተያዘው የበጀት ዓመትም፤ የስታስቲክስ መ/ቤት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ከዘርፉ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ለመሰብሰብ ታቅዷል።

ጃፈር ዓሊ

ነጋሽ መሓመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ