1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊን ግንብ ተገነደሰ-ሕዳር 9 1989

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2002

ተቀናቃኝ ፖለቲከኞቹ በየሚፈልጉ-በየሚያሸንፉበት መንገድ እንዲሆን ከመሻኮት ባለፍ ግን እንዴትና መቼ እንደሚሆን ለየሕዝባቸዉ ትክክለኛዉን መልስ መስጠት አልቻሉም

https://p.dw.com/p/KS7d
ጎርባቾቭና ሜርክል በሃኛዉ አመት በአልምስል AP

እኛ አንድ ሕዝብ ነን።ከ1949 ጀምሮ (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የምሥራቁም የምዕራቡም ሕዝብ አንድነትን ያልጠየቀበት-ሥለ አንድነት ያልዘመረበት ጊዜ በርግጥ የለም።የሁለቱ ወገኖች ፖለቲከኞች የኮሚንስት-ካፒታሊስት ተቃራኒ ደጋፊዎቻቸዉም ሁለት የሆነዉ አንድ የጀርመን ሕዝብ የሚመኝ የሚፈክረዉን በየራሳቸዉ መንገድ መጋራታቸዉ አልቀረም ነበር።ተቀናቃኝ ፖለቲከኞቹ በየሚፈልጉ-በየሚያሸንፉበት መንገድ እንዲሆን ከመሻኮት ባለፍ ግን እንዴትና መቼ እንደሚሆን ለየሕዝባቸዉ ትክክለኛዉን መልስ መስጠት አልቻሉም።የዚያን ቀን ግን በሕዝብ ግፊት ሆነ።የበርሊን ግንብ ተገነደሰ።ዛሬ ሃያ-አመቱ።ለሃያ-አመቱ ያፍታ ቅኝት አብራችሁኝ ቆዩ።

ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ