1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡርቃ ዕገዳ በቤልጂግ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2002

በትንሽቷ አውሮፓዊት ሐገር በቤልጂግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ድምፅ የተሰጠበት አንዳንድ ሙስሊም ሴቶች የሚያዘወትሩትን ሰውነትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍነውን ቡርቃን መልበስ እንዲታገድ የቀረበው ህግ ያለ አንዳች ተቃውሞ አልፏል ።

https://p.dw.com/p/NEKz
ምስል AP

ቡርቃ በአደባባይ እንዳይለበስ ለመከልከል በምክርቤት ደረጃ ድምፅ በመስጠት ቤልጂግ የመጀመሪያዋ አውሮፓዊት ሀገር ሆናለች ። የበርካታ ሙስሊሞች መኖሪያ በሆነችው በፈረንሳይ ደግሞ ማንነትን ይሸሽጋል የተባለውን ቡርቃን በሚለብሱ ላይ ከበድ ያለ ቅጣት የሚጥል ጠንካራ ህግ ተረቋል ። ሁለቱ ሐገራት ቡርቃን በአደባባይ እንዳይለበስ የወሰዱትና ለመውሰድ ያቀዱት ቁርጠኛ ዕርምጃ ፣ የአብዛኛው ዜጎቻቸው ድጋፍ ቢኖረውም ተቃውሞም አልተለየውም ። ቤልጂግና ፈረንሳይ በግንባር ቀደምትነት በቡርቃ እና ዓይንን ጭምር በሚከልለው በኒቃብ ላይ ሲዘምቱ ሌሎች የአውሮፓ ሐገራትም የነርሱን ፈለግ ለመከተል ዳር ዳር እያሉ ነው ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችንም በተለይ የቤልጂግ ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ቡርቃ መልበስ እንዲታገድ ባሳለፈው ውሳኔና በእገዳውን ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች አስተያየት ላይ ያተኩራል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ