1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡሽ መጽሀፍና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አስተያየት

ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2003

የቀድሞው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ዳብልዩ ቡሽ «ዲሲሽን ፖይንትስ» በሚል ርዕስ ሰሞኑን አንድ መጽሀፍ አወጡ።

https://p.dw.com/p/Q6Hr
ምስል KINDLE

ቡሽ እአአ ከ2000 እስከ 2008 ዓም ድረስ በስልጣን ስለነበሩባቸው ዓመታት በሚያስታውሰው መጽሀፋቸው አንዳንድ ስህተት መፈጸማቸውን ቢያስታውቁም፡ ራሳቸውን የሚወቅሱበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል። የዩኤስ አሜሪካ ጸጥታ ኃይል አባላት በቡሽ የስልጣን ዘመን ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን በውኃ ውስጥ እየደፈቁ የመረመሩበት ዘዴ ህገ ወጥ ነው በሚል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቀድሞው ፕሬዚደንት ላይ ክስ እንዲመሰረት ጠይቋል።d

DW

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ