1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ሃያ-ጉባኤ ዉሳኔና ጥያቄዉ

ሰኞ፣ ኅዳር 8 2001

የዋሽንግተን ጉባኤተኞች የችግሩ ትክክለኛ ምክንያት ገና ተመርምሮ መፍትሔዉ እንዲፈለግ መወሰናቸዉ ደግሞ ጉባኤዉ ያጫረዉን ተስፋ-ምኞት በቅዠት እንዳይለዉጠዉ ያሰጋል

https://p.dw.com/p/FwhE
ጉባኤዉምስል AP

የተመራጭ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ጥያቄ ቀና መልስ እንዲያገኝ፣ የተሰናባች ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ ቃል-የምር፣ የቡሽና ቡሽ የሰበሰቧቸዉ መሪዎች ዉል ገቢር እንዲሆን ተስፋ የማያደርግ-የማይመኝ አለም በርግጥ የለም።የጥያቄ፣ ቃሉ፥ የስብሰባ ዉሉ ምክንያት አሜሪካ-ከሰረች አለምም ከሰረ ከመባሉ ባለፍ የኪሳራዉን እዉነኛ ምክንያት አለም አለማወቁ ተስፋ-ምኞቱን በቅዠት እንዳይለዉጠዉ እንጂ ስጋቱ።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የአለም ሐብታም ሐገራት መሪዎች ቅዳሜ ያደረጉትን ጉባኤ አስታከን ምክንያት ዉጤቱን ላፍታ እንቃኛለን አብራችሁኝ ቆዩ።