1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ሰባት ጉባኤ ዉሳኔዎች

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2007

ቡድን ሰባት በመባል የሚታወቁት ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገራት እዚህ ጀርመን ባቫሪያ ግዛት ዉስጥ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቀናት የጀመሩትን ጉባኤ ትናንት አጠናቀዋል።

https://p.dw.com/p/1FeA0
G7 Gipfel Schloss Elmau Outreach Konferenz Gruppenfoto
ምስል Getty Images/AFP/R. Michael

[No title]

ምዕራባዉያኑ መንግሥታት ዐበይት የተባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተነጋገሩ ሲሆን በተለይ በመጪዉ ዓመት ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ ለሚካሄደዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ የምስራች የሚሆን ዉሳኔ ማሳለፋቸዉ ተሰምቷል። መንግሥታቱ ከባቢ አየር ዉስጥ በመከማቸት የመሬትን የሙቀት መጠን እንዲጨምር አድርጓል የሚባለዉ የካርቦንን ልቀት የሚያስከትሉ የኃይል ምንጮችን የመቀነስ ዉሳኔያቸዉ በተግባር ከተገለጸም ታሪካዊ ርምጃ እንደሚሆን ነዉ ታዛቢዎች የሚናገሩት። ከዚህም ሌላ ጉባኤዉ በግሪክ የዕዳ ቀዉስ፤ በምሥራቅ ዩክሬን ብጥብጥና የሩሲያ ጣልቃ ገብነት፤ በስደተኞች መበራከትና በመሳሰሉት ላይም ተወያይተዉ ዉሳኔዎች አሳልፈዋል። ስለኃያላኑ መንግሥታት ስብሰባና ዉሳኔ የበርሊን ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ