1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል መድረክ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 26 2004

የዕለቱ ዝግጅታችን ሰሞወኑን የዶይቼ-ቬለ የባህል ድረ-ገጽ ያተኮረባቸዉን ባህል ነክ ክንዉኖች ልናካፍል ይዘናል፣ የመጀመርያዉ ርዕሳችን የጀርመንኛ ቋንቋ በጀርመን በሚኖሩ መጤዎች ምክንያት ከሌላ ቋንቋ ጋር እየተበረዘ መሆኑን የሚያመለክት ዘገባ ነዉ። ከ 50 አመት ጀመሮ መጤ ዘጎች ወደ ጀርመን ሃገር በሰፊዉ መግባት መጀመራቸዉን በማሳየት ይጀምራል።

https://p.dw.com/p/15iVI
ምስል picture-alliance/dpa

የዕለቱ ዝግጅታችን ሰምወኑን የዶይቼ-ቬለ የባህል ድረ-ገጽ ያተኮረባቸዉን ባህል ነክ ክንዉኖች መረጥ መረጥ አድርገን ልናካፍል ይዘናል፣ የመጀመርያዉ ርዕሳችን የጀርመንኛ ቋንቋ በጀርመን በሚኖሩ መጤዎች ምክንያት ከሌላ ቋንቋ ጋር እየተበረዘ መሆኑን የሚያመለክት ዘገባ ነዉ። ከ 50 አመት ጀመሮ መጤ ዘጎች ወደ ጀርመን ሃገር በሰፊዉ መግባት እና መኖር መጀመራቸዉን በማሳየት ዘገባዉ ሃተታዉን ይጀምራል። ይህም ሁኔታ በጀርመን የማህበረሰቡን የአኗኗር ዜዴ ብቻ ሳይሆን ባህሉንም ቋንቋዉም ላይ ለዉጥ እያሳየ መምጣቱ እሙን መሆኑ ተጠቅሶል። በተለይ በቋንቋዉ ላይ የታየዉን የተለያዩ ለዉጦች አንድ ጀርመናዊ የቋንቋ ፕሮፊሰር ለአመታት ባደረጉት ጥናታቸዉ ተከታትለዋል። ጀርመናዊዉ የቋንቋ ምሁሩ ኡቨ ሃይንሪሽ በምስራቅ ጀርመን ዛክሰን ክፍለ ግዛት ላይፕዚክ ከተማ ዉስጥ በሚገኘዉ ዩንቨርስቲ እዉቅ ምሁር ናቸዉ። ኡቨ ሃይንሪሽ በላይይፕዚክ ዩንቨርስቲ ስለ ጀርመንኛ ቋንቋ በርካታ ምርምን በማካሄዳቸዉም ይታወቃሉ። ኡቨ ሃይንሪሽ በተለይም በጀርመን ከተለያዩ አገሮች የመጡ ዜጎች የትዉልድ ቋንቋቸዉ ከጀርመንኛ ጋር እየቀላቀሉ በመናገራቸዉ በቋንቋዉ ላይ የሚያሳድረዉ ተጽኖ ላይ ጥናት አካሂደዉ ሰፊ ትንታኔን ጽፈዋል። በርግጥ የቋንቋ ምሁሩ በምስራቃዊ ጀርመን፣ ዛክሰን ክፍለ ግዛት በሚገኘዉ በላይፕዚግ ዩንቨርስቲ ይህን ጥናት ቢካሄድም በላይፕዚክ ወይም ባጠቃላይ በዛክሰን ክፍለ ግዛት ይህን አይነት ጥናት በመስክ ለማካሄድ ቦታዉ አመች አለመሆኑ ግልጽ ነዉ። ምክንያቱም ነላይፕዚግ ከተማ የሚገኙት የዉጭ አገር ዜጎች አስር ከመቶ አደማይሞሉ በጀርመን አገር የሚኖሩ የዉጭ አገር ንዋሪዎች ቁጥር መዘርዝር በግልጽ ያሳያል። ከላይፕዚግ ከተማ ይልቅ፣ በበርሊን፣ በፍራንክፉርት፣ በሙኒክ እና በዲስልዶርፍ ከተሞች በርካታ የዉጭ አገር ዜጎች ይገኛሉና ነዉ።
እንደ ቋንቋ ምሁሩ ጀርመናዊ ኡቨ ሃይንሪሽ ትንተና፤ የዉጭ አገር ዜጎች ወይም መጤ ነዋሪዎች የጀርመንኛ ቋንቋን ጠንቅቀዉ ባለማወቃቸዉ በሚነጋገሩበት ግዜ ሳይፈልጉ በትክክል አይናገሩም፤ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጀርምንኛ ቋንቋ በራሱ እጅግ ከባድ ቋንቋ በመሆኑ ነዉ። በጀርመንኛ ቋንቋ ሰዋስዉ ዉስጥ የተለያዩ፣ ግስ፣ እና ተዉላጠ ስም፣ የስሞች የፅኦታ ባህሪ የሚገልጽባቸዉ ቃላት፣ በጀርመንኛዉ der, die, das በእንግሊዘኛዉ Articles የሚባሉት አጠቃቀሞች ይገኛሉ። ታድያ ሰዎች ጀርመንኛ ቋንቋን በሚናገሩበት ግዜ፣ ለምሳሌ ጀርመንኛ ቋንቋ እያንዳንዱ ቃል ፆታ አለዉ። አነስታይ፣ተባታይ፣ እና ግኡዝ። ይህ የቃሉ የፆታ መለያ ካልታወቀ በአንድ ቃል የተስተካከለ አርፍተ ነገር ለመስራት አስቸጋሪ ይሆናል። ለምን ቢባል አርፍተ ነገር በሚሰራበት ግዜ ከስም ፣ ተሳቢና ማሰርያ አንቀፅ ጋር የቃሉ ጦታ ለዉጥ የሚያሳይበት ሁኔታ በመኖሩ ነዉ። በዚህም ጀርመንኛ ቋንቋ በጣም ከባድ ያደርገዋል። ለምሳሌ ያህል እንደገና ልጃገረድ ሴት ሶታን ቢይዝም በጀርመንኛ የግኡዝ ፆታን ይይዛልና ነዉ። ቁሳቁሶችንም ለምሳሌ ማንኪያ ሹካ ቢላ የተለያየ ዞታ ይሰጣቸዋል። ይህ የጀርመንኛ ቋንቋ ናህሪ ነዉ። የቋንቋ ምሁሩ ጀርመናዊ ይህ አይነቱ ችግር ይላሉ ይህ አይነቱ ችግር በጀርመን አገር እንደሚስተዋለዉ፤ በእንግሊዝና እና በፈረንሳይ አገሮች ይህ የቋንቋ መበላሽት አይነት ሁኔታ እንደማይታይ በጥናታቸዉ አመልክተዋል።

Uwe Hinrichs Slavist Universität Leipzig
ጀርመናዊዉ የቋንቋ ምሁሩ ኡቨ ሃይንሪሽምስል Uwe Hinrichs

ለሰላሳኛ ግዜ እየተካሄደ ባለዉ እና ባለፈዉ ሳምንት ለንደን ላይ በደማቅ ትርዒት የጀመረዉ የኦሎምፒክ ዉድድር ሰምወኑን የዶይቼ ቬለ የባህል ድረ-ገጽ ከስፖርት ዉድድሩ ባሻገር የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የዘገበት ርዕሰ ነዉ።

Spanien Barcelona zehnspurige Stadtautobahn
ባርሴሎና ከጎአ 1992 ዓም የኦሎምፒክ ዉድድር በፊትምስል Architekturbüro BAU

ኦሎምፒክ ከአለም አገራት የተሰባሰቡ ስፖርተኞች በተለያዩ ስፖርቶች የሚወዳደሩበት የዉድድር መድረክ ብቻ ሳይሆን የስነ-ጥበብ ክህሎቶች የሚታዩበት ታላቅ መድረክ ለመሆኑ እሙን መሆኑን፣ የዶይቼ ቬለ የባህል ድረ-ገጽ የኦሎምፒክ ዉድድር እና ግንባትዉ በሚለዉ ርዕስ ስር ይዘረዝራል። ምንም እንኳ ያለንበት የጎርጎረሳዉያኑ 2012 ዓ,ም ላይ ብንሆንም ምናልባትም የኦሎምፒክ ጨዋታ ባይኖር ኖሮ የስፔንዋ ባርሴሎና ዛሪ የደረሰችበት ገጽታ ላይ ላትደርስ ትችል ነበር ሲል ሃተታዉን ይጀምራል። እጎአ 1992 ዓም ባርሴሎና 25 ኛዉን የኦሎምፒክ ዉድድር ስታዘጋጅ የከተማዋ መሰረተ ልማት በዘመናዊ መልክ መዋቀሩ እና መሰራቱ ተመልክቶአል። ሜዲተራንያን ባህርን ተንተርሳ የምትገኘዉ ባርሴሎና ከተማ በ18ኛዉ ክፍለ ዘመን ኢንዱስትሪ የበዛባት ባለ አስር ረድፍ የመኪና መንገድ ምንጣፍ የተዘረጋባት እና ከኢንዱስትሪ የሚወጣ ፍሳሽ ወደ ባህር የሚፈስባበት ካናል የተዘረጋባት ከተማ ነበረች። እ,ጎ,አ 1992 ዓ,ም በባርሴሎና የኦሎምፒክ ጨዋታ ከመካሄዱ ቀደም ሲል ከተማዋ ምንም አይነት መስዕብ ያልነበራት ሰዉ ደስ ብሎት ሊኖርበት የማይመርጣት ከተማም እንደነበረች፤ ኦሎምፒክ ጨዋታ ከመካሄዱ በፊት በነበሩት አመታት የከተማዋ ፕላን ቤሮ ዋና ተጠሪ የነበሩት Joan Busquets ያስታዉሳሉ። በዚህም ይላሉ Joan Busquets ስፔን ለዉድድሩ ዝግጅት የባርሴሎና ከተማ የሚያዋስናት ሜዲተራንያን ባህርን እሳቤ በመክተት እና ገጽታዋን ከባህሩ በማቆራኘት ባርሴሎና 92 በሚል ፕሮጄ ከተማዋ በአዲስ ታነጻለች። ቀደም ሲል አስር መኪናን በረድፍ የሚያስተናገድበትና ከተማዋን በስፋት ይዞ የነበረዉ የተንጣለለ አዉሮጎዳን በማጥበብ፣ የከተማ አዉቶቡስ እና ባቡር መጓጓዣ መሃል ከተማ ላይ በዘርጋት የተለያዩ የመኖርያ ቤቶች እና መስብ ያላቸዉ መንደሮች ፣የመዝናኛ ጠበብ ጠብ ያሉ ፓርኮችን በመስራት እንዲሁም ወደ ባህሩ የሚወስዱ የእግረኛ መንገዶችን በመዘርጋት፤ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች ባርሴሎናን ወደ ሚያዋስናት ወደ ሜዲተራንያን ባህሩ ዳርቻ በእግር በቀላሉ እንዲደርሱ የእግረኛ መንገድ ዉብ በሆነ ሁኔታ በማንጠፍ ታነጸ። ታድያ ባርሲሎና ከተማ እ,አ 1992 የኦሎምፒክ ጨዋታ መስተንግዶዋ በኋላ ዛሪ በሜዲተራንያን ባህር ላይ የተንጣለለች በርካታ የአለም ህዝብ የሚጎበኛት ተወዳጅ ከተማ ለመሆን በቅታለች። ባርሴሎና በጎርጎረሳዉያኑ 1992 ዓ,ም ኦሎምፒክን ለማዘጋጀት በተሰጣት የፋይናንስ ድጎማ ከተማዋ መሃል የነበረዉ ስቴዲዮም እጅግ ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ ታንጾ፣ ከዝግጅቱ በኋላ የባርሴሎናዉ ስቴዲዮም የተለያዩ አገሮች እዉቅ የእግር ኳስ ቡድኖች ተወዳጅ የመጋጠምያ ቦታም ሆንዋል። በዚህም ባርሴሎና ከአነስተኛ ከተማነት በ1992 ዓ,ም 25 ኛዉን የኦሎምፒክ ዉድድር ካዘጋጀች በኋላ ታዋቂዋ የአዉሮጳ አንዷ ታላቅ ከተማ ለመሆን በቅታለች።

Spanien Strand in Barcelona
ባርሴሎና ከኦሎምፒኩ ዝግጅት በኋላምስል DW

ዛሪ ለንደን 30ኛዉን የኦሎምፒክ ጨዋታ ስታካሄድ ከባርሴሎናዉ ለየት የሚያደርገዉ ለዚሁ የኦሎምፒክ ጨዋታ አንድ የከተማዋን መንደር በአዲስ መሰራቱ ነዉ። ቀደም ሲልም Stratford የተሰኘዉን የከተማዋን ክፍል በአዲስ ለማነጽ በርግጥ እቅድ ተይዞ ነበር። የኦሎምፒክ ጨዋታዉን አስታኮ ይህ ኢስት ኤንድ የለንደን ከተማ ክፍል በፍጥነት በአዲስ ባይሰራ ኖሮ ምናልባትም እንደ እቅዱ 40 አመት ሊወስድ ይችል እንደነበር በለንደን የኦሎምፒክ ዝግጅት ቢሮ ተጠሪ Klaus Grewe ገልጸዋል።

ከመካከለኛዉ ክፍ ለዘመን ጀምሮ በእንግሊዝ ማህበረሰብ ዘንድ East end በመባል የሚጠራዉ ቦታ የእንጨት ማጠራቀምያ ፣ ቆሻሻ የሚተላለፍበት ቦይ፤ አልያም የቆሻሻ ማጠራቀምያ የሚል መጠርያ ተሰጥቶት ቆይቶአል። ግን አሁን ይህ ቦታ የአለም ግዙፉ የስፖርት መድረክ ኦሎምፒክ ማዕከል ሆንዋል። ይህ የከተማ ክፍል ከኦሎምፒክ ኮሚቴ የድጎማ ገንዘብ ያገኘዉ መዘጋጃ ቤቱ ቦታዎችን ለማስተካከል እና ለማሳመር መንገዶችንም ለመስራት በነበረዉ እቅድ እንደነበርም ተመልክቶአል። አሁን የኦሎምፒክ ዉድድር የሚስተናገድበት የዝያን ግዜዉ የኢንዱስትሪ እና የፋብሪካ ቦታ ሲጸዳ፤ 2 ቢሊዮን አፈር እና ቆሻሻ ከቦታዉ ተነስቶ፤ በምትኩ በርካታ ዛፎች እና ልዪ ልዪ አበባዎች ተተክለዋል። የኦሎምፒኩ የዋና፤ የቅርጫት ኳስ የዉድድር ቦታዎች አና የተመልካች ሰገነቶች ተገንብተዋል። ከአለም ዙርያ ከሚገኙ 204 አገራት የመጡ ስፖርተኞች 28 ያህል የስፖርት አይነቶችን የሚወዳደሩበት ይህ ቦታ የኦሎምፒክ ዉድድሩ ሲፈጸም በሰፊዉ የተሰራዉ የስፖርት መወዳደርያ ቦታ አነስ እንደሚደረግ አልያም ግዙፉ የመዋኛ ቦታ ጨርሶ ሊነሳ እንደሚችል ተነግሮአል። በአንፃሩ ግዙፉ የቅርጫት ኳስ መወዳደርያ አዳራሽ በለንደን ለሚኖሩ ለሰርገኞች በተለይ የሰርግ ድግሳቸዉን በሰፊዉ ለሚደግሱት ለህንዶች እና ለፓኪስታን ዜጎች ለበኪራይ እንደሚሰጥም ተጠቅሶአል።

Deutschland Ausstellung Marilyn Monroe The last sitting in Paderborn
የሆሊዉድዋ ብርቅ እና ድንቅዪ ሜርሊን ሞንሮምስል Bert Stern 2012

በሌላ በኩል የለንደኑ ኦሎምፒክ ከመጀመሩ ከወራቶች በፊት ጀምሮ፤ በስቴዲዮም ዙርያ የነበሩ ጥቃቅን ሱቆች መዘጋታቸዉ በግዴታ በመወረሳቸዉ፤ የቤት ክራይ ዋጋ መጨመሩ፣ የትራንስፖርት እጥረት መከሰቱ፤ በተለይ በለንደን ያለ ነዋሪን ኦሎምፒክን እንዲጠላ እንዲያማርር ሳያደርገዉ እንዳልቀረ ተዘግቦአል። ሌላዉ 1972 የጀርመናዋ ሙኒክ ከተማ ኦሎምፒክ ስታዘጋጅ የከተማዋን መሰረተ ልማቶች መስተካከላቸዉ እና በጥሩ መገንባታቸዉ ይታወሳል። ታድያ እንደሙኒኩም ሆነ እንደ ባርሴሎናዉ የኦሎምፒክ ዝግጅትም ሆነ ጥሩ የከተማ ግንባታ ሁሉ የለንደኑ ኦሎምፒክ 2012 ዉድድር እና East End በሚል መጠርያ የሚታወቀዉን የከተማዋን ክፍል ስም እንደሚያድስለት እሙን ነዉ።

ሌላዉ የዶይቸ ቬለ ድረ-ገጽ የዛሪ ሃምሳ አመት ከዚህ አመት በሞት የተለየችዉ የሆሊዉድዋ ብርቅ እና ድንቅ የፊልም ተጫዋች ሜርሊን ሞንሮን የሙት ቀን በማሰብ የፊታችን እሁድ እንደሚታሰብ በማሰብ ዘገባ አቅርቦአል። እዚህ ራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ክፍለ ግዛት ፓደርቦን ከተማ ዉስጥ Last sitting በተሰኘ ሞንሮ ለመጨረሻ ግዜ በህይወትዋ ዘመን የተነሳቻቸዉ ፎቶግራፎች ለህዝብ ለዕይታ ይቀርባሉ። የሆሊዉድዋ ዉቢት በመባል የምትታወቀዋ አሜሪካዊትዋ የፊልም ተዋናይ፥ የፎቶ ሞዴል ፤ ሙዚቀኛ፤ የዛሪ ሃምሳ አመት በ 36 አመትዋ መኝታ ቤትዋ ነበር ሞታ የተገኘችዉ። ሞንሮ ከዚህ አለም በሞት ከተሰናበተች ከሃምሳ አመት በኋላም ዛሪም ተወዳጅነትዋና ዝናዋ አልቀነሰም። በፈረንሳይ ካን ዘንድሮ በተካሄደዉ የፊልም ፊስቲቫል ላይ ምስልዋን የሚያሳየዉ እጅግ ግዙፍ ፎቶ ቀርቦ በፊስቲቫሉ ተወስታለች፤ በቀጣይ በአለማቀፍ የፊልም ስራ እንቅስቃሴ ላይ እንደ ትልቅ አርማ ህያዉ ትወሳለች። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ