1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል መድረክ

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2005

የዶቼ ቬለ የጀርመንኛዉ ቋንቋ ክፍል ባህልና ትምህርት በሚል ርዕስ ከሚያወጣዉ ተከታታይ ጽሁፍ ዉስጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ወጣት ተመራማሪዎች የቋሚ ስራ ችግር የሚያሳየዉን ዘገባና፣ የጀርመን ጦር በዉጭ አገሮች ለሰላም ማስከበሩ ሂደት በሚያደርገዉ ተልዕኮ፤ የሚሰጠዉን ን የባህል ትዉዉቅ ሰሚናር በጥቂቱ እንቃኛለን።

https://p.dw.com/p/16Bps
ምስል Getty Images

በጀርመን በተለያየ የትምህርት መስክ በዶክተርነት ማዕረግ ለመመረቅ የጥናት ስራቸዉን የሚሰሩ 200, 000 ያህል ዜጎች ይገኛሉ። ከነዚህ ምሁራን መካከል 80 በመቶዉ እጩ ዶክተሮች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልያም ከዩንቨርስቲ ዉጭ ባሉ የምርምር ተቋማት ዉስጥ በስራ መስክ ላይ የሚገኙ ናቸዉ። ለምሳሌ በጀርመን ታዋቂ ከሆነዉ ሄልምሆልትዝ አልያም ከማክስ ብላንክ የምርምር ተቋም ዉስጥ ሊሆን ያችላል። ቢሆንም ግን እነዚህ ወጣት ምሁራን በነዚህ ተቋማት ዉስጥ ስራ አግኝተዉ ለመቀጠር ሲቸገሩ ይታያል። ከዉጭ የሚመጡ ምሁራንም እንዲሁ በጀርመን ስራ የማግኘት ዕድላቸዉ የመነመነ ነዉ ። በተለይም በስነ-ልቦና ትምህርት አልያም በህብረተሰብ ጥናት መስክ የዶክትሪት መመረቅያ የጥናት ስራቸዉን በመስራት ያሉ ወጣት ምሁራን ከአንድ አመት ላነሰ ግዜ የሚሆን የስራ ኮንትራትን ቢበዛ የግማሽ ቀን ስራን ነዉ የሚያገኙት። በዚህም ምክንያት ወጣት የምርምር ስራ ምሁራን ረዘም ላለ ግዜ የስራ ኮንትራትን አግኝተዉ ቤተሰብን የመመስረት እድላቸዉ የተመናመነ ነዉ። በጀርመን የቤተሰብ ጉዳይ እና የምርምር ተቋም የስራተኛ ማህበር ለዶክትሪት ማዕረግ፤ በድህረ ምረቃ ላይ ለሚገኙ እና የዶክትሪት ማዕረግን ላገኙ ምሁራን እንዲሁም ከዉጭ ለሚመጡ ምሁራን የተሻለ የስራ ዕድልን ለማመቻቸት ተዘጋጅቶአል። በዉጭ የሚገኙ ምሁራንንም ወደ ጀርመን አገር ለመሳብ እና አገር ዉስጥ ያሉትንም ተመራማሪዎች እዚሁ በምርምር ስራ ላይ እንዲቆዪ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ሁለተኛዉ ርዕሳችን የሌሎችን ባህልን መቀበል እና ማወቅ ይሰኛል፤ የጀርመን ጦር እ,ጎ,አ ከ1990 ጀምሮ በዉጭ አገሮች ግዳጆችን እና ተልኮን መፈጸም መጀመሩ የሚታወቅ ነዉ። ጦሩ በሚዘምትበት አገር ተልኮዉ ሰላም እና የጸጥታ ሁኔታዎችን ማስከበር ነዉ። ወታደሮቹ የዘመቱበትን አገር ባህል አዉቀዉ፤ በአገሩ ላይ የተሻለ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እና ህብረተሰቡን መረዳት እንዲችሉ፤ የጦር መኮንንኖችን የሚሄዱበት አገር ህብረተሰብ ባህል እኗኗር በማስተማር በቀጣይ መኮንኖቹ ለወታደሮች ገለጻ እንዲያደርጉላቸዉ በመደረግ ላይ ነዉ። በጀርመን በራይን ላንድ ክፍለ ግዛት ኮብሌንዝ ከተማ በሚገኘዉ የጀርመን ጦር ሃይል ማዕከል ዉስጥ ለ20 መኮንኖቹ የባህል ትዉዉቅ ሰሚናር ላይ የዶቼ ቬለዉ ጉንተር ቢርክን ስቶክ ተገኝቶ የጀርመን ጦር የባህል ትዉዉቅ በሚል ርዕስ ዘገባ አጠናቅሮአል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ