1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል መድረክ

ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2003

የጥበብ ፈርጦች ይታሰቡ በሚል ርእስ ባለፈዉ ሳምንት ታዋቂዉን የባህላዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ ይርጋ ዱባለን በማስታወስ የባህላዊ ሙዚቃ ተጫዋቾችን እና በኢትዮጽያ የባህላዊ ሙዚቃን በመድረክ እንዲወጣ ካደረጉ ባለሞያዎች ጋር ቃለ መጥይቅ ያደረግንበት መሰናዶ ዛሪ በሁለተኛዉ ክፍል

https://p.dw.com/p/RShW
በቮርዝ ቡርግ ከተማ የአፍሪቃ ፈሲቫልምስል DW

የይርጋ ዱባለን ቃል ከማህደሩ ይዞ የሙዚቃ አዋቂ ባለሞያዎችን አነጋግሮአል። በቅድያ ሰሞኑን በጀርመን የባህል ጽረ-ገጾች ያተኮሩባቸዉን አጠር አጠር ያሉ ዜናዎችን ያቀርባል። ለቅንብሩ አዜብ ታደሰ መልካም ቆይታ

ለሃያ ሶስተኛ ግዜ እዚህ በጀርመን በቮርዝ ቡርግ ከተማ የተካሄደዉ አለማቀፉ የአፍሪቃ ፈሲቫል ባለፈዉ እሁድ ተጠናቆአል። በየአመቱ ከአፍሪቃ አገራት የተለያዩ ከያንያን የሚሳተፉበት የቮልስቡርጉ የአፍሪቃ የሙዚቃ ፊስቲቫል ዘንድሮ በተለይ የካረቢክ አገራትን ሙዚቃ ሰፋ ባለ መድረክ አስተዋዉቆአል።

ፊስቲቫሉ ዘንድሮ የጀመረዉ ከአፍሪቃዊትዋ ደሴት አገር ከትሪኒዳድ ቶቤጎ ከመጡት አዛዉንት በከያኒ ካሊፕሶ ሮዘ ነዉ። ካሊፕሶ ሮዘ በአለም ላይ ተወዳጅ የሆነዉን ካሊፕሶን ሙዚቃ የጻፉ ናቸዉ። ከያኒዋ እስካሁን ስምንት መቶ በላይ ሙዚቃን መድረሳቸዉ ተነግሮላቸዋል። በአዉሮጻ ትልቅ እንደሆነ የሚነገርለት አለማቀፍ የአፍሪቃ ፊስቲቫል በዝግጅቱ በየአመቱ የአፍሪቃ አገሮችን ሙዚቃን በማስተዋወቅ የአዉሮጻ አገራትን የተለያየ ባህል በማሳየት ለሶስት ቀናት ይዘልቃል። በቮርዝ ቡርግ ከተማ የዛሪ ሃያ ሁለት አመት የጀመረዉ ይህ የአፍሪቃ ፊስቲቫል በየአመቱ ወደ እዚህ ከተማ የአፍሪቃን የሙዚቃ ትርኢት እና ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያን ለማየት ከተለያዩ የአዉሮጻ አገራት በርካታ ታዳሚዎችንም ያሰባስባል። ባለፈዉ እሁድ በተጠናቀዉ የአፍሪቃ የሙዚቃ ፊስቲቫል ላይ በደቡብ ጀርመን በነበረዉ ነጎድጓዳማ ዝናብ አዘል የአየር ጸባይ ምክንያት ብዙ ተመልካች ባይገኙም በዘንድሮ በተካሄደዉ የሶስት ቀን ፊስቲቫል ላይ በአጠቃላይ ሰማንያ ሶስት ሽህ እንግዶች መገኘታቸዉ ተገልጾአል።
ሌላዉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የተጠናቀቀዉ እና ለአምስት ቀናት የዘለቀዉ የወንጌላዊት ቤተክርስትያን ቀን ሰምዎኑን የጀርመን የባህል ድረ- ገጾች ሰፋ ባለ አምዳቸዉ የተለያዩ ክስተቶችን ዘግበዋል። በቤተክርስትያን እገዛ አለመቋቋሙ የሚነገርለት የቤተክርስትያን ቀን ዝግጅት በጀርመን ሃኖቨር ከተማ እ.አ ከ1949 አ.ም ጀምሮ ህብረተሰብን በማሰባሰብ በተለያዩ ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያል፣ ለችግሮች መፍትሄ ያፈላልጋል። በየሁለት አመቱ የሚካሄደዉ የወንጌላዊት ቤተክርስትያን ቀን ዘንድሮ በምስራቅ ጀርመንዋ ከተማ ድሪስደን የተካሄደ ሲሆን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ለአምስት ቀናት በሁለት ሽህ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ማወያየቱ ተገልጾአል። ለምሳሌ በሃይል ምንጭ፣ በሰላም ጥረት፣ በጀርመን የአቶም ሃይል ምንጭን የመዘጋት ጥረት፣ የጀርመናዉያን በዉጭ አገር የተልኮ ዘመቻ፣ ወደ ጀርመን መጠለያ ጣብያ የሚመጡ ስደተኞች በግዳጅ ወደ የመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን በመቃወም በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ፖለቲከኞችን፣ የሚመለከታቸዉን የማህበረሰብ አባላትን፣ በማወያየቱ የዘንድሮዉ የወንጌላዊት ቤተክርስትያን ቀን ከምንግዜዎም በላይ ፖለቲካዊ የቤተክርስትያን ቀን ተብሎለታል። ድሪስደን ከተማ በኤልበን ወንዝ ዳርቻ የተካሄደዉ ለየአምስት ቀናቱ የቤተክርስትያን ቀን ዝግጅት የተፈጥሮ ሁናቴም ረድቶት ጥሩ ብራማና እና ሞቃታማ ቀናት ላይ በመዋሉ ዝግጅቱ መቶ ሃያ ሽህ ህዝብን እንዳሰባሰበ ተገልጾአል። በዚህም ከአስራ ስድስት አመት ወዲህ ይህን ያህል ህዝብ ሲሰባሰብ የመጀመርያ እንደሆነም ተገልጾአል።
ሌላዉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ሰላሳ አንድ ቻይናዉያን ጥንዶች የባቫርያዉ ንጉስ ሉድቪግ ቤተ-መንግስት እንደ ንጉሳዊ ቤተሰብ ደንብ ጋብቻቸዉን መፈጸማቸዉ አንዱ የጀርመንን የባህል ድረ-ገጽን የሳበ ርዕስ ነበር። በባቫርያዉ ንጉስ ሉድቪግ ቤተ-መንግስት የሰርግ ቀናቸዉን ለመፈጸም በየአመቱ በርካታ ቻይናዉያን የሚመጡ ሲሆን የአብዛኞች ቻይናዉያን ምኞት በህይወታቸዉ አንድ ግዜ በንጉስ ሉድቪግ ቤተ መንግስት ጋብቻቸዉን መፈጸም ነዉ። በቻይና ከሰርግ ድግስ በፊት የጋብቻ ፊርማን ለማስቀመጥ ሙሽሪት እና ሙሽራዉ ፖሊስ ጣብያ ሄደዉ ዉላቸዉን በህግ ፊት ማኖር እንዳለባቸዉ ባለፈዉ ሳምንት ትዳራቸዉን ከፈጸሙት ሰላሳ አንድ ጥንዶች መካከል አንዳንዶቹ አልደበቁም። ሰላሳ አንዱ ቻይናዉያን በጥንት አይነቱ የንጉሳዊ የጋብቻ ስነ-ስርአት አይነት ሰርግን በጀርመኑ በባቫርያዉ ንጉስ ቤተ-መንግስት ለመፈጸም እና ለአስር ቀናት እንደ ንጉስ እንደ ንግስት ለመስተናገድ ሙሽሪት እና ሙሽራዉ አስር ሽህ ይሮ መክፈል ይኖርባቸዋል። ያም ሆነ ይህ በንጉሳዊ ደንብ በሰረገላ በወርቅ ዙፋን ተንቆጥቁጠዉ የተስተናገዱት ሰላሳ አንድ ቻይናዉያን ጥንዶች ወደ ጀርመን ከመምጣታቸዉ በፊት በቻይና ህግ ጋብቻቸዉን ፖሊስ ጣብያ በመሄድ መፈራረማቸዉን ሳይገልጹ አላለፉም።

Jorge Semprun
ታዋቂዉ የስፓኝ የስነ-ጽሁፍ ሰዉ ዮርግ ዜፕሩን
Schloss Neuschwanstein Chinesische Hochzeiten
31 ቻይናዉያን ጥንዶች በባቫርያዉ ንጉስ ሉድቪግ ቤተ-መንግስት የሰርግ ድግስምስል dapd
NO FLASH Evangelischer Kirchentag 2011 in Dresden
የወንጌላዊት ቤተክርስትያን ቀን በምስራቅ ጀርመንዋ ከተማ ድሪስደንምስል DW

በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት በምስራቅ ጀርመን በቱሪንገን የፊደራል ክልል የሚገኘዉ ቡህን ቫልድ የናዚ የአይሁዳዉያን ማጎርያ ጣብያን አልፈዉ ታዋቂ የስነ-ጽሁፍ ስራዎችን የትያትር እና የፊልም ድርሰቶችን ለአለም ያበረከቱ የስፓኝ ዜጋ ዮርግ ዜፕሩን ከትናንት በስትያ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸዉ በባህል ድረ-ገጽ የሰፈረ ርእስ ነዉ። ፖለቲከኛ፣ የስነ-ጽሁፍም ሰዉ አይደለሁም የሚሉት የ 87 አመቱ ዜፕሩን የስነ-ጽሁፍ ስራቸዉ በስፓኝ በነበረዉ በጀነራል ፍራንኮ አንባገነናዊ አገዛ ለህትመት ባለመብቃቱ ምክንያት አብዛኛዉን ስራቸዉን በፈረንሳየኛ እየጻፉ በፈርንሳይ አገር ነበር ለህትመት ያበቁት። እስፓኙ ደራሲ በህጻንነታቸዉ በስፔን የነበረዉን የእርስ በርስ ጦርነት ኖረዋል፣ ከዝያም ጀርመን ፈረንሳይን ስትወጋ የፓሪስ ነዋሪ ነበሩ፣ በጀርመንም ቢሆን በናዚ ጦር በማጎርያ ጣብያ ታስረዉ ኖረዋል፣ በዚህም ነዉ የህይወት ታሪካቸዉን ጋዜጠኛ ፍራንሲስካ አጉስቲን ዮርግ ዜፕሩን የሃያኛዉን ክፍለ ዘመን ዋንኛ የአዉሮጻ የታሪክ ማህደር ስትል የገልጻቻቸዉ። የጀርመንን ባህል እንደሚወዱ፣ የስፓኝም የፈንሳይም ዜጋ እንዳልሆኑ ግን አዉሮጻዊ እንደሆኑ የገልጹት የስነ-ጽሁፍ ሰዉ እ.አ 1994 አ.ም ከጀርመን የመጽሃፍ አሳታሚዎች ማህበር የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ከሌላ የአዉሮጻ አገራት ይልቅ በጀርመን ታዋቂ የሆኑት ዜፕሩን ሽልማትን ከጀርመን እጅ ሲያገኙ ለጀርመን ያለኝ ፍቅር ከጀርናዉያንም በኩል መልስ አገኘሁ ሲሉ መግለጻቸዉ ተዘግቦአል።

ባለፈዉ ሳምንት ወደ ጀመርነዉ ርእሳችን ስንመለስ የባህል አንባሳደሩ ይርጋ ዱባለ ከአስር አመት በፊት የሰጡንን ቃለ መጠይቅ ይዘን በኢትዮጽያ የባህል ሙዚቃ ስራ ዙርያ የሚሰሩ ምሁራንን እና ከያንን ይዘን የጥበብ እንቁዎች ያላቸዉን እዉቀት ለትዉልድ እንዲያስተላልፉ በህይወት ባሉ ግዜ እንዲታሰቡ ምን መደረግ አለበት ስንል የጀመርነዉን መሰናዶአችንን እንቀጥላለን፣ ይርጋ ዱባለ በማዜማቸዉ የኢትዮጽያን ባህላዊ ሙዚቃ መሳርያ ማሲንቆን በመጫወታቸዉ ብቻ አይደለም የሚታወቁት ገጣሚም ናቸዉ። ያድምጡ!፡

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ