1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህል መድረክ

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 5 2003

የካሜሩናዊትዋ የጥበብ ንግስት ይላል ሰሞኑን በዶቸ ቬለ የባህል ድረ-ገጽ ላይ የሰፈረዉ ርዕስ።

https://p.dw.com/p/RkxO
የካሜሩን የጥበብ ማዕከል በዶዉላ ከተማምስል DW

በካሜሩን የዛሬ መቶ አመት ጀምሮ ወደ ነበረዉ ታሪክ መለስ የሚያደርገዉ ይህ ርዕስ በጥንት ግዜ የካሜሩን ንጉስ ቅምቅም አያቷ እንደሆኑ የተነገረላት አንዲት የኪነ ጥበብ ሰዉ በአሁንዋ ካሜሩን ከተማዎች ስነ ጥበብን እና ታሪክን በማጣመር ትምህርታዊ እንዲሆን ማስቻልዋን ያትታል። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ ከ 1884 እስከ 1919 አ.ም ድረስ በጀርመን ቅኝ ግዛት ሥር የነበረችዉ ካሜሩን በዚያ ወቅት ማለ ከመቶ አመታት በፊት በጀርመናዉያኑ ቀኝ ገዥዎች የተገደሉት የካሜሩን ንጉስ ቅምቅም አያቷ የሆኑት Marylin Douala-Bellበአሁኑ ግዜ ለአገርዋ በጥበብ ረገድ አዲስ ምእራፍን ለመክፈት የምታደርገዉን እንቅስቃሴ ያስቃኛል። የዶቸ ቬለዋ አባያ ባህ ከንጉሥ ዘር የተገኘችዉ ካሜሩናዊት የምትሰራቸዉን ለየት ያሉ እና ያልተለመዱ የጥበብ ስራዎች ቃኝታ እንዲህ ዘግባዋለች። የለቱ የባህል መድረክ ሰሞኑን የዶቼ ቬለ የባህል ድረ-ገጽ በስፋት ካተኮረባቸዉ ርእሶች መካከል የካሜሩኗን የጥበብ ንግስት የሚመለከተዉን ጥንቅር ሰብሰብ አድርገን ሌሎች ባህል ነክ ዘገባዎችን አካተን ይዘን ቀርበናል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ