1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባራክ ኦባማ ዓመታዊ የመርህ ንግግር

ረቡዕ፣ ጥር 18 2003

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አሜሪካ በዓለም ውስጥ ያላትን ቀዳሚ ስፍራ ለመጠበቅና በውድድር ውስጥ ለማሸነፍ ፣ በፈጠራና በሳይንስ መስክ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባት አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/QvdX
ባራክ ኦባማምስል AP
ፕሬዝዳንት ኦባማ በትናንትናው ምሽት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ባሰሙት ዓመታዊ የመርህ ንግግራቸው ትኩረታቸው የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ማሳደግ እዳዋን መቀነስና በትምሕርትና በሳይንስ ላይ መሆኑን አስረድተዋል ። በአሜሪካን የሚገኙ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ጉዳይ እልባት እንዲያገኝም ጠይቀዋል ። በተለመደው የሪፐብሊካኖችና የዲሞክራቶች የአቀማመጥ ረድፍ ሳይሆን ተሰባጥረው በመቀመጥ ህብረታቸውን ላሳዩት የአሜሪካን የህዝብ እንደራሴዎች የህዝቡ ፍላጎት ጎን ለጎን መቀመጣቸው ብቻ ሳይሆን አብረው መስራታቸው መሆኑንን ተናግረዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ። አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ ሽዋዬ ለገሰ