1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የባቫሪያ (ባየር) ግዛት ልዑክ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 8 2011

በግዛቲቱ ጠቅላይ ሚንስትር በዶክተር ማርኩስ ዘደር የተመራዉ የመልክተኞች ቡድን ትናንት ለኢትዮጵያዉያንና አዲስ አበባ ለሚኖሩ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶች የእራት ግብዣ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3GsfG
ÄthiopienAddis Abeba Bayern-Abend
ምስል DW/Getachew Tedla Haile Giorgis

የባቫሪያ ምሽት

Freistaat Bayern –(የባየር ወይም በእንግሊዝኛ ባቫርያ ነፃ አስተዳደር እንደማለት ነዉ-) ተብሎ የሚጠራዉ የደቡባዊ ጀርመን  ግዛት ባለስልጣናትና ባለሐብቶች ሠሞኑን ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነዉ።በግዛቲቱ ጠቅላይ ሚንስትር በዶክተር ማርኩስ ዘደር የተመራዉ የመልክተኞች ቡድን ትናንት ለኢትዮጵያዉያንና አዲስ አበባ ለሚኖሩ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶች የእራት ግብዣ አድርጓል።የባየር ምሽት በተባለዉ ድግስ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነርና የጋባዦቹ መልዕክተኞቹ መሪ ዶክተር ማርኩስ ዘደር በየተራ ባሰሙት ንግግር መልዕክተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት በሐገሪቱ የሚደረገዉን ለዉጥ በቅርብ ለማየት ነዉ።ባየር በቆዳ ስፋት ከ16ቱ የጀርመን ክፍለ ግዛቶች የመጀመሪያዉን ደረጃ የያዘች ሐብታም ግዛት ናት።በሕዝብ ብዛት ደግሞ ከኖርድ ራይን ቬስት ፋለን ቀጥሎ ሁለተኛ ናት።

Deutschland München Markus Söder
ምስል picture-alliance/dpa/P. Kneffel

ጌታቸዉ ተድላ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ