1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባን ኪሙን የሩዋንዳ ጉብኝት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 4 2002

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባንኪሙን ሩዋንዳን ስላስቆጣው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዘኛው ምህፃር የ UNHCR ረቂቅ ዘገባ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የጀመሩት ውይይት እንደሚቀጥል አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/P7rO
ባን ኪሙንምስል AP

ትናንት ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ካጋሜ ጋር የተነጋገሩት ባን እንዳሉት ፕሬዝዳንት ካጋሜ ውይይቱን ለመቀጠል ተስማምተዋል ። ባን በሰጡት መግለጫ ሩዋንዳ ፣ የዳርፉር የሰላም ተልዕኮዋን እንዳታቋርጥም ተማፅነዋል ። የሩዋንዳ መንግስት በበኩሉ ባን ኪሙን በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ኪጋሊ ድረስ በመምጣታቸው መርካቱን አስታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ