1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች አቤቱታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 24 2013

ምዕራብ ወለጋ መንዲ እና አካባቢዉ የሠፈሩ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ባለማግኘታቸዉ ለችግር መጋለጣቸዉን አስታወቁ።በሰዳል ወረዳ የተፈጠረዉን ግጭት ሸሽተዉ ምዕራብ ወለጋ የገቡት ተፈናቃዮች ወደ ሶስት ሺሕ ይጠጋሉ።

https://p.dw.com/p/3uIsJ
Äthiopien Vertreibung und Massaker in der Region West-Benishangul Gumuz
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

ተፈናቃዮቹ ምግብ፣ መድሐኒትና መጠለያ አላገኙም

ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ሰዳል ወረዳ የተከሰተዉን የፀጥታ መታወክ ሸሽተዉ  ምዕራብ ወለጋ መንዲ እና አካባቢዉ የሠፈሩ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ባለማግኘታቸዉ ለችግር መጋለጣቸዉን አስታወቁ።በሰዳል ወረዳ የተፈጠረዉን ግጭት ሸሽተዉ ምዕራብ ወለጋ የገቡት ተፈናቃዮች ወደ ሶስት ሺሕ ይጠጋሉ። የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ በስልክ ያነጋገራቸዉ ተፈናቃዮች እንደሚሉት ባለፈዉ ሚያዚያ መጀመሪያ ከየቀያቸዉ ከተፈናቃሉ ወዲሕ ምግብ፣መድሐኒትም ሆነ መጠለያ አግኝተዉ አያዉቁም።የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ባለስልጣናት እንዳሉት መስሪያ ቤታቸዉ በክልላቸዉ ለሰፈሩ ተፈናቃዮች እንጂ ከክልሉ ዉጪ ኦሮሚያ ክልል ለሠፈሩ ተፈናቃዮች ርዳታ የማቅረብ ኃላፊነትም ሕጋዊ መብትም የለዉም።

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ