1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫው ቀን እንዲራዘም መጠየቃቸው

ረቡዕ፣ ነሐሴ 26 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል እና ሌሎች የክልሉ ስፋራዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ቦርዱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ኮማንድ ፖስት ጋር ትናንት ነሐሰ 24/2013 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/3zmIt
Assosa Town Äthiopien
ምስል DW/N. Dessalegn

የምርጫ ጉዳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች  በመጪው መስከረም 20/2014 ዓ.ም ምርጫ እንደሚካሄድ አሳውቋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል እና ሌሎች የክልሉ ስፋራዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ቦርዱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ኮማንድ ፖስት ጋር ትናንት ነሐሰ 24/2013 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ከተሳተፉት የቦሮ ዶሞክራቲክ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ ፓርቲያቸው ሰላም በሌለበት የሚካሄድ ምርጫ ተአማኒነት የጎደለው በመሆኑ ምርጫው እንዲራዘም ለቦርዱ ማመልከቱን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የቤኒሻጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፌት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው በምርጫ ቦርድ በሚወጣው መርሀ ግብር መሰረት በክልሉ ምርጫ መካሄድ አለበት የሚል ሀሳብ አቅርበዋል። የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ በዚህ ጉዳይ ላይ የምርጫ ቦርድ ሀሳብ ለማካተት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ