1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሉዝ ሙዚቃ መነሻ ማሊ ይሆን?

እሑድ፣ ኅዳር 13 2002

እዚህ በአዉሮጻ ተወዳጅነትን ያገኙት የማሊ የሙዚቃ አቀንቃኞች በባህላዊ የሙዚቃ መሳርያቸዉና በዜማ ልዩ ቅላጼአቸዉ ታዋቂነትን በማትረፍ ላይ ያሉ ይመስል።

https://p.dw.com/p/Kcnh
የማሊዉ ሙዚቀኛ ባዙኩ ኩቴምስል Thomas Dorn

እንደዉም ሰሞኑን በጀርመን የባህል ድረ-ገጽ እዉነት ብሉዝ የተሰኘዉ የሙዚቃ አይነት መነሻዉ ከማሊ ይሆን የሚለዉን ጥያቄ ይዞ የማሊን ጥንታዊ ባህላዊ የሆነዉን የሙዚቃ መሳርያ በትልቅ ለጥፎ የሚታይ ጽሁፍም ወጥቶአል። እዉነት ብሉዝ የሙዚቃ አይነት መነሻዉ ከማሊ ይሆን?
የማሊ ልዩ የባህል ዜማን አንጉራሪ እና ባህላዊዉን ክራር መሰል ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች አሊ ፋኩ ቱሪ እጅግ ጥንታዊዉን የሙዚቃ መሳርያ አንድ እዉነተኛ የአፍሪቃ አልማዝ ይለዋል ሌላዉ እንዲሁ በማሊ እጅግ ታዋቂ የሆነዉ ሙዚቀኛ ብሉዝ የተሰኘዉ የሙዚቃ ቃና መገኛዉ ማሊ መሆኑን በማስረገጥ ይገልጻል።
በማሊ እጅግ ጥንታዊነቱ የሚነገርለት ባህላዊዉ የሙዚቃ መሳርያ Ngoni ይሰኛል። በአይነቱ የኛን ክራር ይመስላል። በምዕራባዊቷ ማሊ Ngoni የተሰኘዉ ሙዚቃ በጥንት ግዜ ወንዶች በአደን ወቅት የሚጫወቱበት የሙዚቃ መሳርያም እንደሆነ ይነገራል። ከዚሁ የሙዚቃ መሳርያ ጋር በተያያዘ Griot የተሰኘዉ ባህላዊዉ የዜማ ስልት ነዉ። በምዕራብ አፍሪቃ አገሮች በተለይ ደግሞ በማሊ ይህንን ዜማ በማዜም ከቅም ቅም አያት እየወረደ የሚመጣ እና አባት ለልጅ ልጁ እያወረሰ የሚያዜሙት የሙዚቃ ስልት ነዉ።
ባዙኩ ኩቴ ማሊያዊዉ እዉቅ ሙዚቀኛ ይህንኑ የባህል መሳርያ ከሚጫወቱ ቤተሰቦች ነዉ የመጣዉ የሙዚቃ መሳርያዉን ሲጫወት ሲያዜምም ነዉ ለአካለ መጠን የደረሰዉ። በማሊ ተወላጆች ዘንድ ክብር ያለዉ ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያን ለመማር እንዲሁም ለመጫወት ባዙኩ ኩቴ አባት ቤት የማይመጣ ሙዚቃ አፍቃሪ አልነበረም። አስከፊ በነበረዉ በቅኝ ግዛት ዘመን የገባዉ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳርያም ሆነ የዜማ ስርአት በመለወጡ ምክንያት ባህላዊዉ የማሊ የሙዚቃ መሳርያ እንዳይጠፋ የሚጥሩት አዛዉንቶች ጥቂት እንዳልሆኑም ኩቴ ይገልጻል። በመቀጠል ባዙኬ ኮቲ በቀድሞ ግዜ ይላል ስለ ማሊ ጥንታዊ ክራር መሰል ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ በጥንት ግዜ አባቶቻችን እና አያቶቻችን የሙዚቃ መሳርያዉን ተቀምጠዉ ነበር የሚጫወቱት ታድያ በነሱ ዘመን የነበረዉ የክራር ገመድ ሶስት ወይም አራት ብቻ ነበር፣ አሁን ግን እስከ ዘጠኝ ክር ማለት የሙዚቃ ቃና ማዉጫ ገመድ አለዉ እንዳይከብደንም ማንጠልጠያ አበጅተልነታል።
ይህንኑ የሙዚቃ መሳርያ በኤሌትሪክ እንዲጫወት በማድረግ የቀየረዉ ባዚኮ ኮቴ በአገሩ በርካታ ሙዚቃ አዋቂዎች በመጀመርያ ላይ የማይሆን ነገር ነዉ ብለዉ እንዳልተቀበሉት ይናገራል። ከጥቂት ግዜ በኻላ ይህንኑ የሙዚቃ መሳርያ በመያዝ I speek Fula የተሰኘዉን አልብም አዉጥቶ ከተጫወተ ባኻላ በርካታ የዚህ ባህላዊ ሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾች ስራዉን አድንቀዉ እንደተከተሉት እና በርካቶች ይህንኑ ፈለግ ይዘዉ እንደሚገኙ ተናግሮአል።
በቅርቡ እዚህ በጀርመን አገር የሙዚቃ ድግስዋን ስታሳይ የከረመችዉ የማሊ ተወላጅ ሮክያ ቱሪ ባህላዊዉን እና ዘመናዊ የተባለዉን ሙዚቃ በማዜም ለሌሎች ዜጎች ለጆሮ እንዲጥም አድርጋ ያቀረበችዉ ይመስላል። ሮክያ የማሊን ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ መጫወት ባትችልም ዘመናዊዉ ጊታር ግን ልታዜም ወደ መድረክ ስትወጣ አልተለያትም፣ ያም ሆኖ ግን የሙዚቃዉ ቃና እንዲጥም የሚያደርገዉ ባህላዊዉ የማሊ ክራር መሰሉ ኖጎኒ እንደሆነ ትገልጻለች
«በመጀመርያ ጊታር መጫወትን ነዉ የቻልኩት እናም አስር አመት ሙሉ በባህላዊ የዜማ ቅላጼ በባህላዊዉ ጊታር እያዜምኩ ነዉ የታጀብኩት አሁን ከሶስት አመት ወዲህ ግን አዲስ ነገር መስራትን ስላሰብኩ ባህላዊዉን የማሊን የብሉዝ ቅኝት ይዤአለሁ»
በማሊ ባንባራ በሚባለዉ ቋንቋ የሚያዜሙት ዜማ በምዕራብ አፍሪቃዎቹ አገሮች በርግጥ ተደማጭነታችዉ እጅግ የላቀ ሲሆን አሁን በአዉሮጻ ደግሞ ተወዳጅነቱ እየጎላ መጥቶአል። ምንም እንኻ የባንናራ ቋንቋ ተናጋሪ እጅግ ጥቂት ቢሆንም ወይም የለምም ለማለት ቢያስደፍርም።
የማሊያዋ አቀንቃኝ ሮክያ ምንም እንኻ ቤተሰቦችዋ ሰበብ ብዙዉን ህይወትዋን በምዕራቡ አገር አሳልፋ የጃዝ የክላሲክ እንዲሁም የሮክ የሙዚቃ አይነት ተጽኖ አድርጎባት የአገርዋን ባህላዊ የሙዚቃ አይነት አድትተዉ እንዳላደረጋት ትገልጻለች። «ቶች ማንጪ የሙዚቃ አልብም በአገሪ በባንባራ ቋንቋ የተዜመ ሲሆን እኩልነት የሚል ስያሜን ይሰጣል። ሙዚቃዉ በአፍሪቃን እና በምዕራቡ አለም በወቅቱ ያለዉን ግንኙነት በተለይ ደግሞ በቀድሞ ቅኝ ገዚ አገሮች እና በአፍሪቃ በቅኝ ግዛት ወድቀዉ በነበሩ አገሮች መካከል ያለዉን ያልጠበቀ ግንኙነት በመንቀፍ ይተርካል።
ሮክያ በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች የዜማ ድግስዋን አቀርባ በርካታ ሙዚቃ አፍቃሪዎችን ልብ ስባለች፣ እናም ታድያ በአስራ ዘጠነኛዉ ምዕተ አመት መጨረሻ በሃያኛዉ ምዕተ አመት መጀመርያ ላይ በሰሜን አሜሪካ ባሉ በአፍሮ አሜሪካኖች ብቅ እንዳለ የሚነገርለት ብሉዝ የሙዚቃ ስልት እዉነት መነሻዉ ከማሊ ይሆን የሚል ጥያቄን አስነስቶአል። በማሊ ዋና ከተማ በባማኮ ነዋሪ የሆነዉ እዉቁ የማሊ ባህል መሳርያ ተጫዋች አሊ ፋኩ ቱሪ ኒጎኒ የተሰኘዉን ጥንታዊዉን የማሊ የሙዚቃ መሳርያ አንግቦ በተለይ በኦስትርያ እና በጀርመን በድጋሚ የሙዚቃ ድግሱን እንደሚያቀርብ እየተነገረለት ነዉ። ታድያ በመድረክ ላይ ሲቀርብ የአገሩን የባህል ልብስ አድርጎ የሙዚቃ መሳርያዉን እየቆረቆረ ሲያዘም በሙዚቃዉ የተማረኩት ምዕራባዉያን በመድረክ ያነሱትን ፎቶ ከጎን አስቀምጠዉ እዉነት ብሉስ ሙዚቃ የመጣዉ ከማሊ ይሆን? ሲሉ በጋዜጣቸዉ ርዕስ በመስጠት ይጽፉለታል።

Bassekou Kouyate
ምስል Thomas Dorn

አዜብ ታደሰ