1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ ፈተና እና ተፈታኞች

ዓርብ፣ ግንቦት 29 2006

ኢትዮጵያ ውስጥ ወቅቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ተማሪዎች ፈተና የሚወዱበት ነው። ፈተና ያጠናቀቁ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እፎይ ብለው ውጤታቸውን በሚጠባበቁበት ሰዓት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጨረሻዎቹን ቀናት በጥናት ተያይዘውታል።

https://p.dw.com/p/1CDNs
Bibliothek in der Matola Schule
ምስል Jessica Scheweleit

«የብሔራዊ ፈተናዎች እና ተፈታኞች» የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕስ ነው።

የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ነበሩ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጡትን ፈተናዎች ባለፈው ሳምንት መውሰድ የጀመሩት፤ ኃላም 12ኛ ክፍሎች ተከትለው፤ ፈተናውን ትናንት አጠናቀዋል። ከ10ኛ ክፍል ተረታኞች አንዱ አዲስ ይባላል። ወጣቱ ጥሩ ውጤት አምጥቶ እንደሚያልፍ ባለሙሉ ተስፋ ነው። አዲስም ይሁን ጓደኞቹ ትንሽ ከሂሳብ ፈተና በቀር በተቀሩት ፈተናዎች ደስተኛ እንደነበሩ ነው ወጣቱ የገለፀልን። እንደ አዲስ ግን ለ12ኛ ክፍል ፈተናዋ ስታጠና የቆየችው፤ተማሪ ፋና ኪዳነ ማሪያም ትባላለች።

እንደ አዲስ እና ፋና ዘና ብላ እረፍቷን ያልጀመረችውና ያሏትን ጥቂት ቀናት በጥናት የምታሳልፈው የ8ኛ ክፍል ተማሪዋ ህይወት ናት። በሚገባ ተዘጋችቻለሁ ትላለች ህይወት። ይህን ለማለት ያበቃትንንና ያደረገችን የጥናት ቅድመ ዝግጅት አጫውታናለሁ።

ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኢጀንሲ የኮሚኒኬሽን አስተባባሪ አቶ ረዲ ሽፋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስለተሰጡት የዘንድሮው የብሔራዊ መልቀቂያ ይዘት፣ ተፈታኞች ብዛት እና አሰራር የገለፁልን አለ።

የድምፅ ዘገባውን ተጭነው ይስሙ!

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ